በረዶውን እንደ ፍርፋሪ ያወርዳል፤ ቅዝቃዜውንስ ማን ይቋቋማል?
እግዚአብሔር ትሑታንን ከፍ ያደርጋል፤ ክፉዎችን ግን ወደ ምድር ይጥላል።
ጌታ የተዋረዱትን ያነሣል፥ ክፉዎችን ግን እስከ ምድር ድረስ ያዋርዳል።
ትሑታንን ከፍ ከፍ ያደርጋል፤ ክፉ አድራጊዎችን ግን በምድር ላይ ጥሎ ያዋርዳቸዋል።
እግዚአብሔር በሕዝቡ ደስ ብሎታልና፥ የዋሃንንም በማዳኑ ከፍ ከፍ ያደርጋልና።
ከኀጢአተኞች ጋር ነፍሴን፥ ከደም ሰዎችም ጋር ሕይወቴን አትጣላት።
ወዳጆቼም ባልንጀሮቼም ባላጋራ ሆኑኝ፥ ከበውም ደበደቡኝ፥ ዘመዶቼም ተስፋ ቈርጠው ተለዩኝ።
እናንተ ፍርዱን የጠበቃችሁ የምድር ትሑታን ሁሉ፥ እግዚአብሔርን ፈልጉ፣ ጽድቅንም ፈልጉ፥ ትሕትናንም ፈልጉ፣ ምናልባት በእግዚአብሔር ቍጣ ቀን ትሰወሩ ይሆናል።
በምሠራበት ቀን በደለኞች ከእግራችሁ ጫማ በታች አመድ ይሆናሉና እናንተ ትረግጡአቸዋላችሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
የዋሆች ብፁዓን ናቸው፤ምድርን ይወርሳሉና።
በጌታ ፊት ራሳችሁን አዋርዱ፤ ከፍ ከፍም ያደርጋችኋል።
ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ።
እንግዲህ በጊዜው ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኀይለኛው ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ፤
ችግረኛውን ከመሬት ያነሣዋል፤ ምስኪኑንም ከጕድፍ ያነሣዋል፤ ከሕዝቡ መኳንንት ጋር ያስቀምጠው ዘንድ፥ የክብርንም ዙፋን ያወርሰው ዘንድ።