መዝሙር 138:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ አንተ እነሆ፥ የቀድሞውንና የኋላውን ሁሉ ዐወቅህ፤ አንተ ፈጠርኸኝ፥ እጅህንም በላዬ አደረግህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔር ክብር ታላቅ ነውና፣ ስለ እግዚአብሔር መንገድ ይዘምሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጌታም መንገድ ይዘምራሉ፥ የጌታ ክብር ታላቅ ነውና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስላደረግኸው ድንቅ ነገር ሁሉና ስለ ታላቅ ክብርህ ይዘምሩልሃል። |
አቤቱ፦ በአማልክት መካከል አንተን የሚመስል ማን ነው? በቅዱሳንም ዘንድ እንደ አንተ የከበረ ማን ነው? በምስጋና የተደነቅህ ነህ፤ ድንቅንም የምታደርግ ነህ፤
እነሆ፥ ባሪያዎች ሐሤት ያደርጋሉ፤ እናንተ ግን ከልባችሁ ኀዘን የተነሣ ትጮኻላችሁ፤ መንፈሳችሁም ስለ ተሰበረ ወዮ! ትላላችሁ።
ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፣ በየስፍራውም ለስሜ ዕጣን ያጥናሉ፥ ንጹሕም ቍርባን ያቀርባሉ፣ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ጌታችን ኢየሱስም ይህን ነገር ተናግሮ ዐይኖቹን ወደ ሰማይ አነሣና እንዲህ አለ፥ “አባት ሆይ፥ ሰዓቱ ደርሶአልና ልጅህ ያከብርህ ዘንድ ልጅህን አክብረው፤
በጨለማ ውስጥ “ብርሃን ይብራ” ያለ እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት የክብሩን ዕውቀት ብርሃን በልባችን አብርቶልናልና።
ከዚህ በኋላ በሰማይ “ሃሌ ሉያ! በዝሙትዋ ምድርን ያጠፋችይቱን ታላቂቱን ጋለሞታ ስለ ፈረደባት፥ የባሪያዎቹንም ደም ከእጅዋ ስለ ተበቀለ፥ ፍርዶቹ እውነትና ጽድቅ ናቸውና ማዳንና ክብር ኀይልም የአምላካችን ነው፤” ብሎ ሲናገር እንደ ብዙ ሕዝብ ታላቅ ድምፅ ያለ ድምፅን ሰማሁ።