ሌዋውያኑም ኢያሱና ቀድምኤል፥ እንዲህ አሉ፥ “ቆማችሁ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም አምላካችንን እግዚአብሔርን አመስግኑ። የከበረ ስሙንም አመስግኑ፤ በበረከትና በምስጋናም ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ አድርጉት።”
መዝሙር 106:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ያዳናቸው፥ ከጠላቶቻቸው እጅ ያዳናቸው ይናገሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለ እግዚአብሔር ታላቅ ሥራ ማን ሊናገር ይችላል? ምስጋናውንስ ሁሉ ማን ተናግሮ ይጨርሳል? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታን ታላላቅ ሥራዎች ማን ይናገራል? ምስጋናውንስ ሁሉ ማን ያሰማል? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ ያደረጋቸውን ታላላቅ ነገሮች ማን ቈጥሮ ሊደርስባቸው ይችላል? የሚገባውንስ ያኽል ሊያመሰግነው የሚችል ማን ነው? |
ሌዋውያኑም ኢያሱና ቀድምኤል፥ እንዲህ አሉ፥ “ቆማችሁ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም አምላካችንን እግዚአብሔርን አመስግኑ። የከበረ ስሙንም አመስግኑ፤ በበረከትና በምስጋናም ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ አድርጉት።”
እነሆ ይህ የመንገዱ ክፍል ነው፤ የቀሩትንም ነገሮቹን እንሰማለን፤ በሚያደርግበትስ ጊዜ የነጐድጓዱን ኀይል የሚያውቅ ማን ነው?”
የእግዚአብሔር ባለጠግነት፥ ጥበብና ዕውቀት እንዴት ጥልቅ ነው! ለመንገዱም ፍለጋ የለውም፤ ፍርዱንም የሚያውቀው የለም።
በክርስቶስ እንደ አደረገው እንደ ከሃሊነቱ ታላቅነት በምናምን በእኛ ላይ የሚያደርገው የከሃሊነቱ ጽናት ብዛት ምን እንደ ሆነ ታውቁ ዘንድ ነው።