ምሳሌ 8:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከብር ይልቅ ትምህርትን፥ ከተፈተነ ወርቅም ይልቅ ዕውቀትን ተቀበሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከብር ይልቅ ምክሬን፣ ከንጹሕ ወርቅ ይልቅ ዕውቀትን ምረጡ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተግሣጼን እንጂ ብርን አትቀበሉ፥ ከተመረጠ ወርቅም ይልቅ እውቀትን ተቀበሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከብር ይልቅ ምክሬን ምረጡ፤ ከንጹሕ ወርቅ ይልቅ ዕውቀትን ምረጡ። |
ጴጥሮስም፥ “ወርቅና ብር የለኝም፤ ያለኝን ግን እሰጥሃለሁ፤ እነሆ፥ በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሥተህ ሂድ” አለው።
ኀዘንተኞች ስንሆን ዘወትር ደስተኞች ነን፤ እንደ ድሆች ስንሆን ብዙዎችን እናበለጽጋለን፤ ምንም የሌለን ስንሆን ሁሉ በእጃችን ነው።