እግዚአብሔር ያያልና፥ ደስም አያሰኘውምና፥ ቍጣውን ከእርሱ ይመልሳል።
አለዚያ እግዚአብሔር ይህን አይቶ ደስ አይለውም፤ ቍጣውንም ከርሱ ይመልሳል።
ጌታ ይህንን አይቶ እንዳያዝንብህ፥ ቁጣውንም ከእርሱ ላይ እንዳያነሣ።
በዚህ ነገር ደስ ቢልህ ግን እግዚአብሔርን ታሳዝናለህ፤ እግዚአብሔርም በጠላትህ ላይ የሚያሳየውን ቊጣ ያቆማል።
ጠላትህ ቢወድቅ ደስ አይበልህ፥ በመሰናከሉም አትታበይ።
ክፋትን በሚያደርጉ ሰዎች ደስ አይበልህ፥ በክፉዎችም አትቅና።