ምሳሌ 23:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሣርን እንደሚበላ ይበላል፥ ይጠጣልም፤ ወደ አንተም አታስገባው፥ ከእርሱ ጋርም እንጀራን አትብላ፥ ብላ፥ ጠጣ ይልሃል፥ ልቡ ግን ከአንተ ጋር አይደለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁልጊዜ ስለ ዋጋ የሚያሰላ ሰው ነውና፤ “ብላ፣ ጠጣ” ይልሃል፤ ልቡ ግን ከአንተ ጋራ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በልቡ እንዳሰበ እንዲሁ ነውና፥ ብላ ጠጣ ይልሃል፥ ልቡ ግን ካንተ ጋር አይደለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከልቡ ሳይሆን ምግቡን እንድትተውለት ፈልጎ ለማስመሰል ያኽል “ብላ፥ ጠጣ” ይልሃል። |
የጠራው ፈሪሳዊም ባየ ጊዜ በልቡ ዐሰበ፤ እንዲህም አለ፥ “ይህስ ነቢይ ቢሆን ኖሮ ይህቺ የምትዳስሰው ሴት ማን እንደ ሆነች፥ እንዴትስ እንደ ነበረች ባላወቀም ነበርን? ኀጢአተኛ ናትና።”
ደሊላም፥ “ ‘አንተ እወድድሻለሁ’ እንዴት ትለኛለህ? ልብህ ከእኔ ጋር አይደለም፤ ስታታልለኝ ይህ ሦስተኛ ጊዜህ ነው፥ ታላቅ ኀይልህም በምን እንደ ሆነ አልነገርኸኝም” አለችው።