አባትህና እናትህ በአንተ ደስ ይላቸዋል፥ አንተንም የወለደች ደስ ይላታል።
አባት እናትህ ደስ ይበላቸው፤ ወላጅ እናትህም ሐሤት ታድርግ።
አባትህና እናትህ ደስ ይበላቸው፥ አንተንም የወለደች ደስ ይበላት።
አባትህና እናትህ በአንተ ደስ ይበላቸው፤ እናትህም በአንተ ሐሤት ታድርግ።
ጠቢብ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፤ ሰነፍ ልጅ ግን እናቱን ያሳዝናታል።
አላዋቂ ልጅ ለአባቱ ፀፀት ነው፥ ለወለደችውም ኀዘን ነው።
ልጄ ሆይ፥ ልብህ ጠቢብ ይሁን ልቤን ደግሞ ደስ ያሰኛል፤
ልጄ ሆይ፥ ልብህን ስጠኝ፥ ዐይኖችህም መንገዴን ይጠብቁ።
ዘመዶችዋና ጎረቤቶችዋም እግዚአብሔር ቸርነቱን እንዳበዛላት በሰሙ ጊዜ ከእርስዋ ጋር ደስ አላቸው።