ፍርሀት ሰነፎችን ይጥላል፥ የተቸገሩ ሰዎች ሰውነትም ይራባል።
የሐሜተኛ ቃል እንደ ጣፋጭ ጕርሻ ነው፤ ወደ ሰው ውስጠኛው ክፍል ዘልቆ ይገባል።
የጆሮ ጠቢ ቃል እንደ ጣፋጭ መብል ነው፥ እርሱም እስከ ሆድ ጉርጆች ድረስ ይወርዳል።
የሐሜተኛ ሰው ቃል እንደ ጣፋጭ ምግብ ደስ እያሰኘ እስከ ውስጥ ሰውነት ድረስ ይወርዳል።
እግዚአብሔርን የሚፈልግ አስተዋይ እንዳለ ያይ ዘንድ እግዚአብሔር ከሰማይ የሰው ልጆችን ተመለከተ።
በሐሰት የሚመሰክሩ በሰይፍ ይገድላሉ፤ በአፋቸው ሰይፍ አለና። የጠቢባን ምላስ ግን የቈሰለውን ይፈውሳል።
ጠማማ ሰው ክፋትን ይዘራል፥ የሐሰት መብራት ክፉዎችን ታቃጥላቸዋለች፥ ወዳጆችንም ትለያለች።
የአላዋቂ አፍ ለራሱ ጥፋት ነው፥ ከንፈሮቹም ለነፍሱ ወጥመድ ናቸው።
በሥራው ራሱን የማያድን፥ ራሱን ለሚያጠፋ ወንድም ነው።
በሕዝብህ መካከል በሸንጋይነት አትዙር፤ በባልንጀራህም ደም ላይ አትቁም፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ነኝ።