ጠማማ ልብ ያለው መልካም ነገርን አያገኝም፥ አንደበቱን የሚለዋውጥም በክፉ ላይ ይወድቃል።
ጠማማ ልብ ያለው ሰው አይሳካለትም፤ በአንደበቱ የሚቀላምድም መከራ ላይ ይወድቃል።
ጠማማ ልብ ያለው መልካምን አያገኝም፥ ምላሱንም የሚገለብጥ በክፉ ላይ ይወድቃል።
ጠማማ ልብ ያለው አይበለጽግም፤ አንደበቱ አታላይ የሆነ ሰው ችግር ላይ ይወድቃል።
ለክፋት በዐይኑ የሚጠቃቀስ ለሰው ኀዘንን ይሰበስባል፥ በግልጽ የሚገሥጽ ግን ሰላምን ያደርጋል።
ጠቢብ ዕውቀትን ይሸሽጋል፤ የችኩል አፍ ግን ለጥፋት ይቀርባል።
የጻድቅ አፍ ጥበብን ይናገራል፤ የዐመፀኛ ምላስ ግን ይጠፋል።
ዘመኑ ለክፉዎች አይሆንምና የኃጥኣንም መብራት ይጠፋልና።
ኀጢአተኛ ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ ርኩስ ነውና፤ ከጻድቃንም ጋር አንድ አይሆንም።
እግዚአብሔርን የሚፈራ ዐመፃን ይጠላል፤ ጥልንና ትዕቢትን፥ ክፉ መንገድንም ይጠላል። የክፉ ሰዎችንም ጠማማ መንገድ ጠላሁ።
የጠቢብ ሰው የአፉ ቃል ሞገስ ናት፤ የሰነፍ ከንፈሮች ግን ራሱን ይውጡታል።