ምሳሌ 16:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የንጉሥ ልጅ እንደ ሕይወት ብርሃን ነው፥ በማያስደስቱትም ዘንድ የማታ ደመና ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የንጉሥ ፊት ሲፈካ ሕይወት አለ፤ በጎነቱም ዝናብ እንዳዘለ የበልግ ደመና ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የንጉሥ ፊት ሲፈካ ብርሃን አለ፥ መልካም ፈቃዱም እንደ በልግ ዝናብ ደመና ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የንጉሥ ፈገግታ ሕይወት ነው፤ ከእርሱም ተወዳጅነትን ማግኘት እንደ በልግ ዝናብ ልምላሜን ይሰጣል። |
እንወቀው፤ እናውቀውም ዘንድ እግዚአብሔርን እንከተል፤ እንደ ወገግታም ተዘጋጅቶ እናገኘዋለን፤ በምድርም ላይ እንደ መጀመሪያውና እንደ ኋለኛው ዝናብ ወደ እኛ ይመጣል።
በኋለኛው ዝናብ ጊዜ ከእግዚአብሔር ዘንድ ዝናቡን ለምኑ፣ እግዚአብሔር መብረቅ ያደርጋል፣ እርሱም የበልግ ዝናብን ለእያንዳንዱም በሜዳ ውስጥ ሣርን ይሰጣል።