እግዚአብሔርን በመፍራት የሚገኝ ጥቂት ሀብት እግዚአብሔርን ባለመፍራት ከሚገኝ ብዙ መዝገብ ይሻላል።
እግዚአብሔርን ከመፍራት ጋራ ያለ ጥቂት ነገር፣ ሁከት ካለበት ትልቅ ሀብት ይበልጣል።
ጌታን ከመፍራት ጋር ያለ ጥቂት ነገር ሁከት ካለበት ከብዙ መዝገብ ይሻላል።
ሀብታም ሆኖ በሁከት ከመኖር ድኻ ሆኖ እግዚአብሔርን በማክበር መኖር ይሻላል።
የጠላቶቼ መዘባበቻ አታድርገኝ ብያለሁና፥ እግሬም ቢሰናከል በእኔ ላይ ብዙ ነገርን ይናገራሉ።
የእግዚአብሔር በረከት በጻድቃን ራስ ላይ ሆና ባለጠጋ ታደርጋለች፥ ኀዘንንም ወደ ልብ አታመጣም።
የክፉዎች ዐይኖች ሁልጊዜ ክፋትን ይመለከታሉ፤ ደጋግ ሰዎች ግን ሁልጊዜ ዝም ይላሉ።
የእግዚአብሔር ሥራ ሁሉ ከእውነት ጋር ነው።
ብዙ ደስታ ከሞላበትና ከክርክር ጋር የዐመፃ ፍሪዳ ካለበት ቤት ይልቅ፥ ከሰላም ጋር ደረቅ ቍራሽ ይሻላል።
በድካምና ነፋስን በመከተል ከሁለት እጅ ሙሉ ይልቅ አንድ እጅ ሙሉ በዕረፍት ይሻላል።
“ኑሮዬ ይበቃኛል፤” ለሚለው ግን እግዚአብሔርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነው፤