ምሳሌ 15:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቀና ልብ ዕውቀትን ትፈልጋለች። የአላዋቂዎች አፍ ግን ክፋትን ይናገራል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አስተዋይ ልብ ዕውቀትን ይሻል፤ የሞኝ አፍ ግን ቂልነትን ያመነዥካል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአዋቂ ልብ እውቀትን ይፈልጋል፥ የሰነፎች አፍ ግን በስንፍና ይሰማራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አስተዋይ አእምሮ ያለው ሰው ዕውቀትን ይፈልጋል፤ ሞኞች ግን በድንቊርናቸው ይረካሉ። |
እንግዲህ ልባቸው አመድ እንደ ሆነና እንደ በደሉ፥ ከእነርሱም ነፍሱን ለማዳን የሚችል ማንም እንደሌለ ዕወቁ፤ በቀኝ እጄ ሐሰት አለ” የሚልም እንደሌለ ተመልከቱ።
ኤፍሬም በሐሰት፥ የእስራኤል ቤትና ይሁዳም በተንኰል ከበቡኝ፤ አሁንም እግዚአብሔር ዐወቃቸው፤ ለእግዚአብሔርም ቅዱስ ሕዝብ ተባሉ።
በተሰሎንቄ ካሉትም እነርሱ ይሻላሉ፤ በፍጹም ደስታ ቃላቸውን ተቀብለዋልና፤ ነገሩም እንደ አስተማሩአቸው እንደ ሆነ ለመረዳት ዘወትር መጻሕፍትን ይመረምሩ ነበር።
ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ። ለእርሱ አሁንም እስከ ዘላለምም ቀን ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።