የተባረከች ሰውነት ሁሉ ትጠግባለች፥ ቍጡ ሰው ግን ክፉ ነው።
ለጋስ ይበለጽጋል፤ ሌሎችን የሚያረካም ራሱ ይረካል።
በረከትን የምታካፍል ነፍስ ትጠግባለች፥ ውሃን የሚያጠጣ እርሱ ደግሞ ይረካል።
ለጋስ ሁን፤ ትበለጽጋለህ፤ ሌሎችን እርዳ፤ አንተም ርዳታ ታገኛለህ።
ዐሥር አልጋዎችና ምንጣፎች፥ ዐሥርም ጋኖችና ፊቀኖች፥ የስንዴና የገብስ ዱቄት፥ ስልቅ አተርና ምስር፥
የየራሳቸውን የሚዘሩና የሚያበዙ አሉ፤ እየሰበሰቡ የሚያጐድሉም አሉ።
ጐተራህም እህልን ይሞላል። የወይን መጥመቂያህም ወይን ይሞላል።
እግዚአብሔርን በእውነት በአገኘኸው ሀብትህ አክብረው። ከእውነተኛ ፍሬህም ሁሉ ቀዳምያቱን አግባለት።
ጻድቃን ግን ጥበብን ይመክራሉ፤ ምክራቸውም ትጸናለች።
የሚምሩ ብፁዓን ናቸው፤ይማራሉና።