መምህር የሌላቸው እንደ ቅጠል ይወድቃሉ። በምክር ብዛት ግን ደኅንነት ይኖራል።
በአመራር ጕድለት መንግሥት ይወድቃል፤ የመካሮች ብዛት ግን ድልን ርግጠኛ ያደርጋል።
መልካም ምክር በሌለበት ሕዝብ ይወድቃል፥ በአማካሪዎች ብዛት ግን ዋስትና ይገኛል።
አማካሪ የሌለው መንግሥት ይወድቃል፤ ብዙ አማካሪዎች ሲኖሩ ግን ዋስትና ይገኛል።
አሁንም ነዪ፤ የልጅሽን የሰሎሞንን ነፍስና የአንቺን ነፍስ እንድታድኚ እመክርሻለሁ።
ከአባቱም ሞት በኋላ የአክዓብ ቤት እንዳደረገ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አደረገ፤ ያጠፉት ዘንድ መካሪዎች ነበሩትና።
ማኅበርን የሚያከብሩ ማስተዋልን ገንዘብ ያደርጋሉ። ምክርም በመካሮች ልብ ትኖራለች።
በጎ ዐሳብ ገንዘብ ላደረጋት ሰው የሕይወት ምንጭ ናት፤ የሰነፎች ትምህርት ግን ክፉ ናት።
ዐሳብ በምክር ትጸናለች፥ በመልካምም ምክር ሰልፍ አድርግ።
በአስተዳደር ጦርነት ይደረጋል፤ ርዳታም ከምትመክር ልብ ጋር ይሆናል።