የጻድቅ አፍ ጥበብን ይናገራል፤ የዐመፀኛ ምላስ ግን ይጠፋል።
የጻድቃን አንደበት ጥበብን ያፈልቃል፤ ጠማማ ምላስ ግን ትቈረጣለች።
የጻድቅ አፍ ጥበብን ይናገራል፥ የመጥመም ምላስ ግን ትቈረጣለች።
ደጋግ ሰዎች ጥበብን ይናገራሉ፤ ጠማማ ነገር የምትናገር ምላስ ግን ትቈረጣለች።
የሚያስጨንቁኝም እኔ ብናወጥ ደስ እንዳይላቸው፥
የሕይወት ምንጭ በጻድቃን አፍ ነው፥ የኃጥኣንን አፍ ግን ጥፋት ይከድነዋል።
ብልህ ሰው ከከንፈሩ ጥበብን ያወጣል፤ አእምሮ የጐደለውንም ሰው በበትር ይመታል።
ጠማማ ልብ ያለው መልካም ነገርን አያገኝም፥ አንደበቱን የሚለዋውጥም በክፉ ላይ ይወድቃል።