ወጥመድን ለወፎች በከንቱ የሚያጠምዱ አይደለምና፥
ወፎች ፊት እያዩ ወጥመድ መዘርጋት፣ ምንኛ ከንቱ ነው!
ወጥመድ በወፎች ዐይን ፊት በከንቱ ይተከላልና።
ልትይዘው የምትፈልገው ወፍ እያየህ የምታጠምደው ወጥመድ ዋጋ የለውም።
እርሱም ከምድር እንስሶች ይልቅ፥ ከሰማይም ወፎች ይልቅ የሚለየኝ ነው።
እግሮቻቸው ወደ ክፋት ይሮጣሉና፥ ደም ለማፍሰስም ይፈጥናሉና።
መግደልን የለመዱ እነርሱ ክፋትን ለራሳቸው ይሰበስባሉ። የኀጢአተኞች ሰዎች አወዳደቃቸው ክፉ ነው።
ወደ ወጥመድ እንደሚቸኩል ዎፍ፥ ሳያውቅም ለነፍሱ ጥፋት እንደሚሮጥ።
በሬ ገዢውን አህያም የጌታውን ጋጥ ዐወቀ፤ እስራኤል ግን አላወቁኝም፤ ሕዝቤም አላስተዋሉኝም።”
ሽመላ በሰማይ ጊዜዋን አውቃለች፤ ዋኖስና ጨረባ፥ ዋሊያም የመምጣታቸውን ጊዜ ይጠብቃሉ፤ ሕዝቤ ግን የእግዚአብሔርን ፍርድ አላወቁም።