ፊልጵስዩስ 4:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቅዱሳንም ሁሉ፥ ይልቁንም ከቄሣር ቤተ ሰብእ የሆኑ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቅዱሳን ሁሉ፣ በተለይም ከቄሳር ቤተ ሰው የሆኑት ወገኖች ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቅዱሳን ሁሉ ይልቁንም ከቄሣር ቤት የሆኑቱ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌሎችም አማኞች ሁሉ በተለይም ከሮማው ንጉሠ ነገሥት ቤተሰቦች የሆኑት ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቅዱሳን ሁሉ ይልቁንም ከቄሣር ቤት የሆኑቱ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። |
ሐናንያ ግን መልሶ እንዲህ አለ፥ “አቤቱ፥ ስለዚህ ሰው በኢየሩሳሌም በቅዱሳኖችህ ላይ የሚያደርገውን ክፉ ነገር ሁሉ ከብዙ ሰዎች ሰምቻለሁ።
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፥ የእግዚአብሔር ፍቅር፥ የመንፈስ ቅዱስም አንድነት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን። የመቄዶንያ ክፍል በምትሆን በፊልጵስዩስ ተጽፎ በቲቶና በሉቃስ እጅ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች የተላከው ሁለተኛዉ መልእክት ተፈጸመ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፤ አሜን።