ዘኍል 21:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ዒር ማደሪያ የሚወርድ፥ በሞዓብ ዳርቻም የሚጠጋ የሸለቆዎች ፈሳሾችንም አቆመ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ዔር የሚወስዱት በሞዓብ ድንበርም የሚገኙት የሸለቆች ተረተሮች።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስከ ዔር ማደሪያ የተዘረጋው በሞዓብም ዳርቻ የሚገኘው የሸለቆች ተዳፋት መሬት።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስከ ዔር ከተማና እስከ ሞአብ ወሰን የሚዘልቁት ሸለቆዎች ሸንተረር” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ዔር ማደሪያ የሚወርድ በሞዓብም ዳርቻ የሚጠጋ የሸለቆች ፈሳሽ። |
በሴይር የተቀመጡ የዔሳው ልጆች፥ በአሮዔርም የተቀመጡ ሞዓባውያን እንዳደረጉልኝ፥ አምላካችን እግዚአብሔር ወደሚሰጠን ምድር ዮርዳኖስን እስክሻገር ድረስ በእግሬ ልለፍ።
“እግዚአብሔርም አለኝ፦ እኔ አሮኤርን ለሎጥ ልጆች ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ ከምድሩ ርስት አልሰጣችሁምና ሞዓባውያንን አትጣላ፤ በሰልፍም አትውጋቸው።