እስራኤልም እግዚአብሔር በግብፃውያን ላይ ያደረጋትን ታላቂቱን እጅ አዩ፤ ሕዝቡም እግዚአብሔርን ፈሩ፤ በእግዚአብሔርም አመኑ፤ ባሪያውንም ሙሴን አከበሩ።
ነህምያ 9:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በግብጽም ሳሉ የአባቶቻችንን መከራ አየህ፤ በኤርትራ ባሕርም ሳሉ ጩኸታቸውን ሰማህ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አንተ በግብጽ የአባቶቻችንን ሥቃይ አየህ፤ በቀይ ባሕርም ጩኸታቸውን ሰማህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በግብጽ የአባቶቻችንን መከራ አየህ፥ በቀይ ባሕርም ጩኸታቸውን ሰማህ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አንተ የቀድሞ አባቶቻችን በግብጽ የደረሰባቸውን መከራ አየህ፤ ቀይ ባሕር አጠገብ ሆነው እንድትረዳቸው ያቀረቡትን ልመና ሰማህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በግብጽም ሳሉ የአባታችንን መከራ አየህ፥ በኤርትራ ባሕርም ሳሉ ጩኸታቸውን ሰማህ፥ |
እስራኤልም እግዚአብሔር በግብፃውያን ላይ ያደረጋትን ታላቂቱን እጅ አዩ፤ ሕዝቡም እግዚአብሔርን ፈሩ፤ በእግዚአብሔርም አመኑ፤ ባሪያውንም ሙሴን አከበሩ።
ሂድ የእስራኤልንም ሽማግሌዎች ሰብስብ፤ እንዲህም በላቸው፦ የአባቶቻችሁ አምላክ፥ የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅም አምላክ፥ የያዕቆብም አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተገለጠልኝ፦ መጐብኘትን ጐበኘኋችሁ፤ በግብፅም የሚደረግባችሁን አየሁ፤
በዚያ ቀን ከግብፅ ምድር ወዳዘጋጀሁላቸው፥ ወተትና ማር ወደምታፈስሰው፥ ከምድር ሁሉ ወደምትበልጥ ምድር አወጣቸው ዘንድ እጄን አነሣሁ።
በግብፅ ያሉትን የወገኖችን መከራ ማየትን አይቻለሁ፤ ጩኸታቸውንም ሰምቻለሁ፤ ላድናቸውም ወርጃለሁ፤ አሁንም ና ወደ ግብፅ ሀገር ልላክህ።’
ደግሞም እግዚአብሔር አለ፤ ባሮች አድርገው በሚገዙአቸው ወገኖች እኔ እፈርድባቸዋለሁ፤ ከዚህም በኋላ ይወጣሉ፤ በዚህም ሀገር ያመልኩኛል።’