La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ነህምያ 4:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ደግ​ሞም በዚያ ጊዜ ሕዝ​ቡን፥ “ሁላ​ችሁ ከብ​ላ​ቴ​ኖ​ቻ​ችሁ ጋር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ውስጥ እደሩ፤ በሌ​ሊ​ትም ጠባ​ቂ​ዎች ሁኑ​ልን፤ በቀ​ንም ሥሩ” አል​ኋ​ቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በዚያ ጊዜ ለሕዝቡ፣ “ሌሊት ዘብ በመጠበቅና ቀን ሥራ በመሥራት እንዲያገለግለን እያንዳንዱ ሰው ከነረዳቱ በኢየሩሳሌም ይቈይ” አልኋቸው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዚህን ጊዜ የሥራ ኀላፊዎቹን “በሌሊት ከተማይቱን ለመጠበቅ፥ ቀን ሥራችንን ያለ ሥጋት ለመሥራት እንችል ዘንድ እናንተም ሆናችሁ ረዳቶቻችሁ፥ ሌሊት ሌሊት በኢየሩሳሌም ቈዩ” አልኳቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ደግሞም በዚያ ጊዜ ሕዝቡን፦ ሁላችሁ ከብላቴኖቻችሁ ጋር በኢየሩሳሌም ውስጥ እደሩ፥ በሌሊትም ጠባቂዎች ሁኑልን፥ በቀንም ሥሩ አልኋቸው።

Ver Capítulo



ነህምያ 4:22
3 Referencias Cruzadas  

ሥራ​ው​ንም እን​ሠራ ነበር፤ ከማ​ለዳ ወገ​ግ​ታም ጀምሮ ከዋ​ክ​ብት እስ​ኪ​ወጡ ድረስ እኩ​ሌ​ቶቹ ጦር ይይዙ ነበር።


እኔና ወን​ድ​ሞ​ችም፥ ብላ​ቴ​ኖ​ችም በኋ​ላ​ዬም የነ​በ​ሩት ጠባ​ቂ​ዎች ልብ​ሳ​ች​ንን አና​ወ​ል​ቅም ነበር። ወደ ውኃም ስን​ሄድ መሣ​ሪ​ያ​ች​ንን እን​ደ​ታ​ጠ​ቅን እን​ሄድ ነበር።