La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ማቴዎስ 8:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እኔ ደግሞ ለሌሎች ተገዥ ነኝና፤ ከእኔም በታች ጭፍራ አለኝ፤ አንዱንም ‘ሂድ’ ብለው ይሄዳል፤ ሌላውንም ‘ና’ ብለው ይመጣል፤ ባሪያዬንም ‘ይህን አድርግ’ ብለው ያደርጋል” አለው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እኔ ራሴ የምታዘዛቸው አለቆች፣ ለእኔም የሚታዘዙ የበታቾች አሉኝ፤ ከእነርሱ አንዱን፣ ‘ሂድ!’ ስለው ይሄዳል፤ ሌላውን፣ ‘ና!’ ስለው ይመጣል፤ ባሪያዬንም፣ ‘ይህን አድርግ’ ስለው ያደርጋል።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እኔ ራሴ ከባለሥልጣኖች በታች ነኝ፤ ከእኔ በታች ደግሞ ወታደሮች አሉኝ፤ አንዱን ‘ሂድ’ ስለው ይሄዳል፤ ሌላውን ደግሞ ‘ና’ ስለው ይመጣል፤ አገልጋዬንም ‘ይህን አድርግ’ ስለው ያደርጋል።”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እኔ ራሴ ለባለ ሥልጣኖች ታዛዥ ስሆን፥ ከእኔ በታች የማዛቸው ወታደሮች አሉኝ፤ ከእነርሱ አንዱን ‘ሂድ!’ ስለው ይሄዳል፤ ሌላውንም ‘ና!’ ስለው ይመጣል፤ አገልጋዬም ‘ይህን አድርግ!’ ስለው ያደርጋል።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እኔ ደግሞ ለሌሎች ተገዥ ነኝና፥ ከእኔም በታች ጭፍራ አለኝ፤ አንዱንም፦ ሂድ ብለው ይሄዳል፥ ሌላውንም፦ ና ብለው ይመጣል፥ ባሪያዬንም፦ ይህን አድርግ ብለው ያደርጋል አለው።

Ver Capítulo



ማቴዎስ 8:9
17 Referencias Cruzadas  

እሳ​ትና በረዶ፥ አመ​ዳ​ይና ውርጭ፥ ቃሉን የሚ​ያ​ደ​ርግ ዐውሎ ነፋ​ስም፤


ኢየሱስም ሰምቶ ተደነቀና ለተከተሉት እንዲህ አለ “እውነት እላችኋለሁ፤ በእስራኤል እንኳ እንዲህ ያለ ትልቅ እምነት አላገኘሁም።


የመቶ አለቃውም መልሶ “ጌታ ሆይ! በቤቴ ጣራ በታች ልትገባ አይገባኝም፤ ነገር ግን ቃል ብቻ ተናገር፤ ብላቴናዬም ይፈወሳል።


ሁሉም “ይህ ምንድር ነው? በሥልጣን ርኵሳን መናፍስትን ያዝዛል፤ እነርሱም ይታዘዙለታልና ይህ አዲስ ትምህርት ምንድር ነው?” ብለው እስኪጠያየቁ ድረስ አደነቁ።


በአ​ጠ​ገ​ብ​ዋም ቁሞ ንዳ​ድ​ዋን ገሠ​ጸ​ውና ተዋት፤ ወዲ​ያ​ውም ተነ​ሥታ አገ​ለ​ገ​ለ​ቻ​ቸው።


እኔም እኮ ገዢ ሰው ነኝ፤ ወታ​ደ​ሮ​ችም አሉኝ፤ አን​ዱን ሂድ ብለው ይሄ​ዳል፤ ሌላ​ው​ንም ና ብለው ይመ​ጣል፤ አገ​ል​ጋ​ዬ​ንም እን​ዲህ አድ​ርግ ብለው ያደ​ር​ጋል።”


ዐሥራ ሁለ​ቱ​ንም ሐዋ​ር​ያት ጠራና፦ በአ​ጋ​ን​ንት ሁሉ ላይ፥ ድው​ያ​ን​ንም ይፈ​ውሱ ዘንድ ኀይ​ል​ንና ሥል​ጣ​ንን ሰጣ​ቸው።


አገ​ል​ጋ​ዮች ሆይ በቅን ልብ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በመ​ፍ​ራት እንጂ ለሰው ደስ እን​ደ​ም​ታ​ሰኙ ለታ​ይታ የም​ት​ገዙ ሳት​ሆኑ፥ በሥጋ ጌቶ​ቻ​ችሁ ለሆኑ በሁሉ ታዘዙ።


ባሪያዎች ስለ መድኃኒታችን ስለ እግዚአብሔር የሚሆነውን ትምህርት በሁሉ ነገር ያስመሰግኑ ዘንድ፥ ለገዛ ጌቶቻቸው እንዲገዙ በሁሉም ደስ እንዲያሰኙ፥ ሳይቃወሙና ሳይሰርቁም በጎ ታማኝነትን ሁሉ እንዲያሳዩ ምከራቸው።