ማቴዎስ 15:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰውን የሚያረክሰው ወደ አፍ የሚገባ አይደለም፤ ከአፍ የሚወጣው ግን ሰውን የሚያረክሰው ይህ ነው፤” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰውን የሚያረክሰው ከአፉ የሚወጣው እንጂ ወደ አፉ የሚገባው አይደለም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ አፍ የሚገባው ሰውን አያረክሰውም፤ ከአፍ የሚወጣው ግን ሰውን የሚያረክሰው ይህ ነው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰውን የሚያረክሰው ከአፍ የሚወጣው ነው እንጂ ወደ አፍ የሚገባው አይደለም!” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰውን የሚያረክሰው ወደ አፍ የሚገባ አይደለም፥ ከአፍ የሚወጣው ግን ሰውን የሚያረክሰው ይህ ነው አላቸው። |
የተገዳደርኸው፥ የሰደብኸውስ ማንን ነው? ቃልህንስ ከፍ ከፍ ያደረግህበት፥ ዐይንህንስ ወደ ላይ ያነሣህበት ማን ነው? በእስራኤል ቅዱስ ላይ አይደለምን?
በራሱ ርኩስ የሆነ ነገር እንደሌለ በጌታችን በኢየሱስ ሆኜ ዐውቄአለሁ፤ ተረድቼአለሁም፤ ነገር ግን ማናቸውም ነገር ርኩስ እንደሚሆን ለሚያስብ ያ ለእርሱ ርኩስ ነው።
በመብል ምክንያት የእግዚአብሔርን ፍጥረት አናፍርስ፤ ለንጹሓን ሁሉ ንጹሕ ነው፤ ለሰውስ ክፉው ነገር በመጠራጠር መብላት ነው።
እነዚህ ውሸተኞች መጋባትን ይከለክላሉ፤ አምነውም እውነትን የሚያውቁ ከምስጋና ጋር ይቀበሉ ዘንድ እግዚአብሔር ከፈጠረው መብል እንዲርቁ ያዝዛሉ።
ሌላ ልዩ ትምህርት አታምጡ፤ ልባችሁ በመብል ያይደለ በጸጋ ቢጸና ይበልጣልና፤ በዚያ ይሄዱ የነበሩ እነዚያ አልተጠቀሙምና።