የስምዖንም አማት በንዳድ ታማ ተኝታ ነበር፤ ስለ እርስዋም ወዲያው ነገሩት።
የስምዖን ዐማት በትኵሳት በሽታ ታምማ ተኝታ ነበር፤ ስለ እርሷም ነገሩት፤
የስምዖን አማት በትኩሳት በሽታ ታማ ተኝታ ነበር፤ ስለ እርሷም ነገሩት፤
በቤት ውስጥ፥ የስምዖን ዐማት በንዳድ ሕመም አተኲሶአት ተኝታ ነበር፤ ስለ እርስዋም መታመም ወዲያው ለኢየሱስ ነገሩት።
የስምዖንም አማት በንዳድ ታማ ተኝታ ነበር፥ ስለ እርስዋም ወዲያው ነገሩት።
ኢየሱስም ወደ ጴጥሮስ ቤት ገብቶ አማቱን በንዳድ ታማ ተኝታ አያት፤
ወዲያውም ከምኵራብ ወጥቶ ከያዕቆብና ከዮሐንስ ጋር ወደ ስምዖንና ወደ እንድርያስ ቤት ገባ።
ቀርቦም እጅዋን ይዞ አስነሣት፤ ንዳዱም ወዲያው ለቀቃትና አገለገለቻቸው።
“ታናሽቱ ልጄ ልትሞት ቀርባለችና እንድትድንና በሕይወት እንድትኖር መጥተህ እጅህን ጫንባት፤” ብሎ አጥብቆ ለመነው።
እኅቶቹም፥ “ጌታችን ሆይ፥ እነሆ፥ የምትወደው ታሞአል” ብለው ወደ ጌታችን ኢየሱስ ላኩ።
እንደ ሌሎች ሐዋርያት ሁሉና፥ እንደ ጌታችን ወንድሞች እንደ ኬፋም ከሴቶች እኅታችንን ይዘን ልንዞር አይገባንምን?