የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚህ ወራት በዚህ ሕዝብ ቅሬታ ዓይን ዘንድ ድንቅ ቢሆን፥ በውኑ በእኔ ዓይን ዘንድ ደግሞ ድንቅ ይሆናልን? ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ሉቃስ 9:43 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም ጌታችን ኢየሱስ ባደረገው ተአምራት ሁሉ ሲደነቁ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዎቹም ሁሉ በእግዚአብሔር ታላቅነት ተገረሙ። እርሱ ባደረገው ሁሉ ሰዎች ሁሉ እየተገረሙ ሳሉ፣ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁሉም ከእግዚአብሔር ታላቅነት የተነሣ ተገረሙ። ሁሉም ኢየሱስ ባደረገው ሁሉ ሲደነቁ ሳሉ፥ እርሱ ለደቀ መዛሙርቱ፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቡም ሁሉ የእግዚአብሔርን ታላቅ ኀይል በማየታቸው ተገረሙ፤ ሁሉም ኢየሱስ ባደረገው ነገር በመደነቅ ላይ ሳሉ እርሱ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁሉም ከእግዚአብሔር ታላቅነት የተነሣ ተገረሙ። ሁሉም ኢየሱስ ባደረገው ሁሉ ሲደነቁ፥ |
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚህ ወራት በዚህ ሕዝብ ቅሬታ ዓይን ዘንድ ድንቅ ቢሆን፥ በውኑ በእኔ ዓይን ዘንድ ደግሞ ድንቅ ይሆናልን? ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
በዚያን ጊዜም አየ፤ እግዚአብሔርንም አመሰገነ፤ ተከተለውም፤ ሕዝቡም ሁሉ አይተው እግዚአብሔርን አመሰገኑት።
ሁሉም ደነገጡ፤ እርስ በርሳቸውም ተነጋገሩ፤ እንዲህም አሉ፥ “ይህ ነገር ምንድን ነው? ክፉዎችን አጋንንት በሥልጣንና በኀይል ያዝዛቸዋልና፥ እነርሱም ይወጣሉና።”
እርሱም “እምነታችሁ ወዴት አለ?” አላቸው፤ እነርሱም ፈርተው ተደነቁ፤ እርስ በርሳቸውም፥ “ውኃም ነፋስም የሚታዘዙለት ይህ ማነው?” አሉ።
ሲያመጣውም ጋኔኑ ጣለውና አፈራገጠው፤ ጌታችን ኢየሱስም ያን ክፉ ጋኔን ገሠጸው፤ ልጁንም አዳነው፤ ለአባቱም ሰጠው። ሁሉም ከእግዚአብሔር ታላቅነት የተነሣ አደነቁ።