Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘካርያስ 8:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚህ ወራት በዚህ ሕዝብ ቅሬታ ዓይን ዘንድ ድንቅ ቢሆን፥ በውኑ በእኔ ዓይን ዘንድ ደግሞ ድንቅ ይሆናልን? ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 እግዚአብሔር ጸባኦት እንዲህ ይላል፤ “በዚያ ጊዜ ይህ ለቀረው የእስራኤል ሕዝብ አስደናቂ መስሎ ሊታይ ይችላል፤ ለእኔ ግን አስደናቂ ሊሆን ይችላልን?” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ በዚህ ወራት በዚህ በተረፈው ሕዝብ ዐይን ነገሩ ቢያስደንቅ፥ በውኑ ለእኔ ግን አስደናቂ ይሆናልን? ይላል የሠራዊት ጌታ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 “በእነዚህ ቀኖች ከሕዝቡ ለተረፉት ይህ የማይቻል ነገር ቢመስልም እንኳ በውኑ ለእኔ የማይቻል ነገር አለን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚህ ወራት በዚህ ሕዝብ ቅሬታ ዓይን ዘንድ ድንቅ ቢሆን፥ በውኑ በእኔ ዓይን ዘንድ ደግሞ ድንቅ ይሆናልን? ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar




ዘካርያስ 8:6
13 Referencias Cruzadas  

“እነሆ እኔ የሥጋ ለባሽ ሁሉ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ በውኑ ከእኔ የሚ​ሰ​ወር ነገር አለን?


እርሱ ግን “በሰው ዘንድ የማ​ይ​ቻ​ለው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ይቻ​ላል” አላ​ቸው።


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ሳ​ነው ነገር የለ​ምና”።


አሁ​ንም በጊ​ዜው የሚ​ሆ​ነ​ው​ንና የሚ​ፈ​ጸ​መ​ውን ነገ​ሬን አላ​መ​ን​ኽ​ኝ​ምና ይህ እስ​ኪ​ሆን ድረስ ዲዳ ትሆ​ና​ለህ፤ መና​ገ​ርም ይሳ​ን​ሃል።”


“ወዮ! አቤቱ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ! እነሆ አንተ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን በታ​ላቅ ኀይ​ል​ህና በተ​ዘ​ረ​ጋች ክን​ድህ ፈጥ​ረ​ሃል፤ ከአ​ን​ተም የሚ​ሳን ምንም ነገር የለም።


ንጉ​ሡም በእጁ ተደ​ግ​ፎት የሚ​ቆም የነ​በረ ያ ብላ​ቴና ለኤ​ል​ሳዕ መልሶ፥ “እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ማይ የእ​ህል ሿሿቴ ቢያ​ደ​ርግ ይህ ነገር ይሆ​ና​ልን?” አለው። ኤል​ሳ​ዕም፥ “እነሆ፥ በዐ​ይ​ኖ​ችህ ታየ​ዋ​ለህ፤ ከዚያ ግን አት​ቀ​ም​ስም” አለ።


በውኑ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ሳ​ነው ነገር አለን? የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ እመ​ለ​ሳ​ለሁ፤ ሣራም ልጅን ታገ​ኛ​ለች።”


አለ​ቆች ደግሞ ተቀ​ም​ጠው እኔን አሙኝ፤ ባሪ​ያህ ግን ፍር​ድ​ህን ያሰ​ላ​ስል ነበር።


ኢየሱስም እነርሱን ተመልክቶ “ይህ በሰው ዘንድ አይቻልም፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ሁሉ ይቻላል፤” አላቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios