ሉቃስ 7:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወይስ ምን ልታዩ ወጥታችኋል? ነቢይን ነውን? አዎን፥ እላችኋለሁ፤ ከነቢይም ይበልጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታዲያ ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይን ልታዩ? አዎን፣ እላችኋለሁ፤ ከነቢይም የሚበልጠውን ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወይስ ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይን? አዎን እላችኋለሁ፤ ከነቢይም የሚበልጠውን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታዲያስ ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይ ለማየት ነውን? አዎ፥ እላችኋለሁ፤ እንዲያውም ከነቢይ የሚበልጠውን ለማየት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወይስ ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይን? አዎን እላችኋለሁ፥ ከነቢይም የሚበልጠውን። |
“ኦሪትም ነቢያትም ከጥንት ጀምሮ እስከ ዮሐንስ ድረስ ነበሩ፤ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የእግዚአብሔር መንግሥት ይሰበካል፤ ሁሉም ወደ እርስዋ ይጋፋል።