በዚያን ሰዓት ኢየሱስ ለሕዝቡ “ወንበዴን እንደምትይዙ ሰይፍና ጐመድ ይዛችሁ ልትይዙኝ ወጣችሁን? በመቅደስ ዕለት ዕለት እያስተማርሁ ከእናንተ ጋር ስቀመጥ ሳለሁ አልያዛችሁኝም።
ሉቃስ 4:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መጽሐፉንም አጥፎ ለተላላኪው ሰጠውና ተቀመጠ፤ በምኲራብም የነበሩት ሁሉ ዐይናቸውን አትኲረው ተመለከቱት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም መጽሐፉን ጠቅልሎ ለአገልጋዩ መልሶ ሰጠውና ተቀመጠ፤ በምኵራብ የነበሩትም ሁሉ ትኵር ብለው ይመለከቱት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጥቅል ብራናውንም ጠቅልሎ ለአገልጋዩ መልሶ ከሰጠ በኋላ ተቀመጠ፤ በምኵራብም የነበሩት ሁሉ ትኩር ብለው ይመለከቱት ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ መጽሐፉን አጥፎ ለአስተናባሪው ሰጠውና ተቀመጠ፤ በምኲራቡ የነበሩትም ሁሉ ትኲር ብለው ወደ እርሱ ይመለከቱ ጀመር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መጽሐፉንም ጠቅልሎ ለአገልጋዩ ሰጠውና ተቀመጠ፤ በምኵራብም የነበሩት ሁሉ ትኵር ብለው ይመለከቱት ነበር። |
በዚያን ሰዓት ኢየሱስ ለሕዝቡ “ወንበዴን እንደምትይዙ ሰይፍና ጐመድ ይዛችሁ ልትይዙኝ ወጣችሁን? በመቅደስ ዕለት ዕለት እያስተማርሁ ከእናንተ ጋር ስቀመጥ ሳለሁ አልያዛችሁኝም።
ከሁለቱ ታንኳዎች ወደ አንዲቱ ታንኳ ወጣ፤ ይቺውም ታንኳ የስምዖን ነበረች፤ “ከምድር ጥቂት እልፍ አድርጋት” አለው፤ በታንኳዪቱም ውስጥ ተቀምጦ ሕዝቡን አስተማራቸው።
በጥዋትም ገስግሦ ዳግመኛ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ፤ ሕዝቡም ሁሉ ወደ እርሱ ተሰበሰቡ፤ እርሱም ተቀምጦ ያስተምራቸው ጀመር።
በሰንበት ቀንም ከከተማዉ በር ወደ ባሕሩ ዳር ወጣን፤ በዚያ የጸሎት ቤት ያለ መስሎን ነበርና፤ በዚያም ተቀምጠን፥ በዚያ ለተሰበሰቡ ሴቶች እናስተምር ጀመርን።
ጴጥሮስም ሕዝቡን ባያቸው ጊዜ እንዲህ አላቸው፥ “እናንት የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ ይህን ለምን ታደንቃላችሁ? እኛንስ በኀይላችንና በጽድቃችን ይህን ሰው በእግሩ እንዲሄድ እንዳደረግነው አስመስላችሁ ለምን ታዩናላችሁ?