La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሉቃስ 23:41 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በእ​ኛስ በሚ​ገባ ተፈ​ር​ዶ​ብ​ናል፤ እንደ ሥራ​ች​ንም ፍዳ​ች​ንን ተቀ​በ​ልን፤ ይህ ግን ምንም የሠ​ራው ክፉ ሥራ የለም።”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እኛ ላደረግነው ነገር ቅጣት እየተቀበልን ስለ ሆነ፣ ተገቢ ፍርድ ላይ ነን፤ ይህ ሰው ግን አንዳች ክፉ ነገር አላደረገም።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እኛ ስለ አደረግነው የሚገባንን እየተቀበልን ነው፤ በእኛ ላይ የተወሰነው ትክክለኛ ፍርድ ነው፤ ይህ ሰው ግን ምንም ክፋት አልሠራም፤” ብሎ ገሠጸው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እኛ ባደረግነው በደል ምክንያት የሚገባንን ቅጣት አግኝተናል፤ ይህ ሰው ግን ምንም ጥፋት አላደረገም።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ስለ አደረግነውም የሚገባንን እንቀበላለንና በእኛስ እውነተኛ ፍርድ ነው፤ ይህ ግን ምንም ክፋት አላደረገም ብሎ ገሠጸው።

Ver Capítulo



ሉቃስ 23:41
19 Referencias Cruzadas  

በተ​ጨ​ነ​ቀም ጊዜ አም​ላ​ኩን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈለገ፤ በአ​ባ​ቶ​ቹም አም​ላክ ፊት ሰው​ነ​ቱን እጅግ አዋ​ረደ።


ስለ ክፉ ሥራ​ች​ንና ስለ ታላቁ በደ​ላ​ችን ካገ​ኘን ነገር ሁሉ በኋላ፥ አንተ አም​ላ​ካ​ችን እንደ ኀጢ​አ​ታ​ችን ብዛት አል​ቀ​ሠ​ፍ​ኸ​ንም፤ ነገር ግን ድኅ​ነ​ትን ሰጠ​ኸን።


በየ​ስ​ፍ​ራ​ቸ​ውም ቆመው የአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሕግ መጽ​ሐፍ አነ​በቡ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተና​ዘዙ፤ ለአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ውም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰገዱ።


እርሱም በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ሳለ ሚስቱ “ስለ እርሱ ዛሬ በሕልም እጅግ መከራ ተቀብያለሁና በዚያ ጻድቅ ሰው ምንም አታድርግ፤” ብላ ላከችበት።


ጲላጦስም ሁከት እንዲጀመር እንጂ አንዳች እንዳይረባ ባየ ጊዜ፥ ውሃ አንሥቶ “እኔ ከዚህ ጻድቅ ሰው ደም ንጹሕ ነኝ፤ እናንተ ተጠንቀቁ፤” ሲል በሕዝቡ ፊት እጁን ታጠበ።


“ንጹሕ ደም አሳልፌ በመስጠቴ በድያለሁ፤” አለ። እነርሱ ግን “እኛስ ምን አግዶን? አንተው ተጠንቀቅ፤” አሉ።


የመቶ አለቃም ከእርሱም ጋር ኢየሱስን የሚጠብቁ መናወጡንና የሆነውን ነገር አይተው “ይህ በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነበረ፤” ብለው እጅግ ፈሩ።


ጓደ​ኛ​ውም መልሶ ገሠ​ጸው፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “አንተ በዚህ ፍርድ ውስጥ ሳለህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክ​ህን አት​ፈ​ራ​ው​ምን?


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስ​ንም፥ “አቤቱ፥ በመ​ን​ግ​ሥ​ትህ በመ​ጣህ ጊዜ ዐስ​በኝ” አለው።


በእናንተ በምታምኑ ዘንድ እንዴት ባለ ቅድስናና ጽድቅ ነቀፋም በሌለበት ኑሮ እንደ ሄድን፥ እናንተና እግዚአብሔር ምስክሮች ናችሁ፤


እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል፤


ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም፤ መከራንም ሲቀበል አልዛተም፤ ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤