ጭፍሮችም ይዘብቱበት ነበር፤ ወደ እርሱም ቀርበው ሆምጣጤ አመጡለት።
ወታደሮችም ቀርበው ያፌዙበት ነበር፤ የኮመጠጠ የወይን ጠጅ እየሰጡትም፣
ወታደሮቹም ወደ እርሱ ቀርበው፥ ሆምጣጤም አምጥተው
ወታደሮቹም እንዲሁ አፌዙበት፤ ወደ እርሱም ቀርበው ሆምጣጤ ሰጡት።
ጭፍሮችም ደግሞ ወደ እርሱ ቀርበው ሆምጣጤም አምጥተው፦
በሐሞት የተደባለቀ የወይን ጠጅ ሊጠጣ አቀረቡለት፤ ቀምሶም ሊጠጣው አልወደደም።
ወዲያውም ከእነርሱ አንዱ ሮጠ፤ ሰፍነግም ይዞ ሆምጣጤ ሞላበት፤ በመቃም አድርጎ አጠጣው።
አንዱም ሮጦ ሆምጣጤ በሰፍነግ ሞላ በመቃም አድርጎ “ተዉ፤ ኤልያስ ሊያወርደው ይመጣ እንደ ሆነ እንይ፤” እያለ አጠጣው።
ሄሮድስም ከሠራዊቱ ጋር አቃለለው፤ አፌዘበትም፤ የሚያንፀባርቅ ልብስም አልብሶ ወደ ጲላጦስ መልሶ ሰደደው።