La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሉቃስ 12:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ወደ አደ​ባ​ባይ ወደ ሹሞ​ቹና ወደ ነገ​ሥ​ታቱ፥ ወደ መኳ​ን​ን​ቱም በሚ​ወ​ስ​ዱ​አ​ችሁ ጊዜ የም​ት​ሉ​ት​ንና የም​ት​ና​ገ​ሩ​ትን አታ​ስቡ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ሰዎች ይዘው ወደ ምኵራብ፣ ወደ ገዥዎችና ወደ ባለሥልጣናት በሚያቀርቧችሁ ጊዜ ሁሉ፣ እንዴት ወይም ምን እንደምትመልሱ አትጨነቁ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ወደ ምኵራቦች፥ ወደ ገዢዎችና ወደ ባለ ሥልጣኖች ሲጐትቱአችሁ፥ እንዴት ወይም ምን እንደምትመልሱ ወይም እንደምትናገሩ አትጨነቁ፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“ሰዎች በየምኲራቡ ሲወስዱአችሁ፥ በገዢዎችና በባለሥልጣኖች ፊት ለፍርድ ሲያቀርቡአችሁ ‘ምን እንመልሳለን? እንዴትስ እንናገራለን?’ ብላችሁ አትጨነቁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ወደ ምኵራቦችና ወደ መኳንንቶችም ወደ ገዢዎችም ሲጐትቱአችሁ፥ እንዴት ወይም ምን እንድትመልሱ ወይም እንድትናገሩ አትጨነቁ፤

Ver Capítulo



ሉቃስ 12:11
14 Referencias Cruzadas  

እን​ግ​ዲህ አሁን ሂድ፤ እኔም አን​ደ​በ​ት​ህን አረ​ታ​ለሁ፤ ትና​ገ​ረ​ውም ዘንድ ያለ​ህን አለ​ብ​ም​ሃ​ለሁ” አለው።


ስለዚህ፥ እነሆ፥ ነቢያትንና ጥበበኞችን ጻፎችንም ወደ እናንተ እልካለሁ፤ ከእነርሱም ትገድላላችሁ ትሰቅሉማላችሁ፥ ከእነርሱም በምኵራባችሁ ትገርፋላችሁ ከከተማም ወደ ከተማ ታሳድዳላችሁ፤


“ስለዚህ እላችኋለሁ፤ ስለ ነፍሳችሁ በምትበሉትና በምትጠጡት፥ ወይም ስለ ሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ፤ ነፍስ ከመብል ሰውነትም ከልብስ አይበልጥምን?


ከእናንተ ተጨንቆ በቁመቱ ላይ አንድ ክንድ መጨመር የሚችል ማን ነው?


ስለ ልብስስ ስለ ምን ትጨነቃላችሁ? የሜዳ አበቦች እንዴት እንዲያድጉ ልብ አድርጋችሁ ተመልከቱ፤


እንግዲህ ‘ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን?’ ብላችሁ አትጨነቁ፤


“ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ፤ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል።


ለደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ስለ​ዚህ እላ​ች​ህ​ዋ​ለሁ፤ ለነ​ፍ​ሳ​ችሁ ስለ​ም​ት​በ​ሉ​ትና ስለ​ም​ት​ጠ​ጡት፥ ለሰ​ው​ነ​ታ​ች​ሁም ስለ​ም​ት​ለ​ብ​ሱት አት​ጨ​ነቁ።