ሉቃስ 11:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በስውር ቦታ ወይም ከዕንቅብ በታች ሊያኖራት መብራትን የሚያበራ የለም፤ የሚመላለሱ ሁሉ ብርሃንን ያዩ ዘንድ በመቅረዝዋ ላይ ያኖራታል እንጂ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “መብራት አብርቶ በስውር ቦታ ወይም ከእንቅብ በታች የሚያስቀምጥ ማንም የለም፤ ይልቁን የሚገቡ ሰዎች ብርሃኑን እንዲያዩ በመቅረዝ ላይ ያስቀምጠዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “መብራትንም አብርቶ በስውር ቦታ ወይም ከእንቅብ በታች የሚያኖረው ማንም የለም፤ የሚገቡ ሰዎች ብርሃኑን እንዲያዩ በመቅረዝ ላይ ያኖረዋል እንጂ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “መብራት አብርቶ በስውር ቦታ የሚያስቀምጠው፥ ወይም እንቅብ የሚደፋበት ማንም የለም፤ ይልቅስ ሰዎች ወደ ውስጥ ሲገቡ እንዲታያቸው ከፍ አድርጎ በመቅረዝ ላይ ያኖረዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መብራትንም አብርቶ በስውር ወይም በእንቅብ በታች የሚያኖረው የለም፥ የሚገቡ ሰዎች ብርሃኑን እንዲያዩ በመቅረዝ ላይ ያኖረዋል እንጂ። |
ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፥ “ቀኑ ዐሥራ ሁለት ሰዓት አይደለምን? በቀን የሚሄድ አይሰናከልም፤ የዚህን ዓለም ብርሃን ያያልና።