ዘሌዋውያን 9:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው አሮን ፍርምባዎቹንና ቀኝ ወርቹን በእግዚአብሔር ፊት ለየ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሮንም ፍርምባዎቹንና የቀኝ ወርቹንም ሙሴ ባዘዘው መሠረት፣ የመወዝወዝ መሥዋዕት አድርጎ በእግዚአብሔር ፊት ወዘወዘው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም እንደ ታዘዘው አሮን ፍርምባዎቹንና ቀኝ ወርቹን በጌታ ፊት ለመወዝወዝ ቁርባን ወዘወዘ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፍርምባዎቹንና በስተቀኝ በኩል ያሉትን የኋላ እግሮች ሙሴ ባዘዘው መሠረት በመወዝወዝ ለእግዚአብሔር ልዩ መባ አድርጎ አቀረበው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው አሮን ፍርምባዎቹንና ቀኝ ወርቹን በእግዚአብሔር ፊት ለመወዝወዝ ቍርባን ወዘወዘ። |
ማንም ሰው የሚናገር ቢሆን፥ እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር፤ የሚያገለግልም ቢሆን፥ “እግዚአብሔር በሚሰጠኝ ኀይል ነው” ብሎ ያገልግል፤ ክብርና ሥልጣን እስከ ዘላለም ድረስ ለእርሱ በሚሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።