ኢዮአስም ካህናቱን፥ “ወደ እግዚአብሔር ቤት የሚገባውን የተቀደሰውን ገንዘብ ሁሉ፥ ስለ ነፍሱም ዋጋ የሚያቀርበውን ገንዘብ፥ በልባቸውም ፈቃድ ወደ እግዚአብሔር ቤት የሚያመጡትን ገንዘብ ሁሉና፥
ዘሌዋውያን 27:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መልካምም ቢሆን ክፉም ቢሆን ካህኑ ይገምተው፤ ካህኑም እንደሚገምተው መጠን እንዲሁ ይሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መልካም ቢሆን ወይም ባይሆን፣ ካህኑ ዋጋውን ይወስን፤ የካህኑም ውሳኔ የጸና ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህኑም መልካም ወይም መጥፎ እንደሆነ ይገምተዋል፤ ካህኑም እንደሚገምተው መጠን እንዲሁ ይሁን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካህኑም የእንስሳውን መልካምነት ወይም መጥፎነት ገምቶ ዋጋውን ይወስን፤ ያም ዋጋ የመጨረሻ ይሆናል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መልካምም ቢሆን ክፉም ቢሆን ካህኑ ይገምተው፤ ካህኑም እንደሚገምተው መጠን እንዲሁ ይሁን። |
ኢዮአስም ካህናቱን፥ “ወደ እግዚአብሔር ቤት የሚገባውን የተቀደሰውን ገንዘብ ሁሉ፥ ስለ ነፍሱም ዋጋ የሚያቀርበውን ገንዘብ፥ በልባቸውም ፈቃድ ወደ እግዚአብሔር ቤት የሚያመጡትን ገንዘብ ሁሉና፥
ካህኑ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ የግምቱን ዋጋ ይቈጥርለታል፤ በዚያም ቀን ግምቱን እንደ ተቀደሰ ነገር ለእግዚአብሔር ይሰጣል።