ዘሌዋውያን 27:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መልካሙን በክፉ፥ ክፉውንም በመልካም አይለውጥ፤ እንስሳንም በእንስሳ ቢለውጥ እርሱና ልዋጩ የተቀደሱ ይሆናሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰውየው መልካም የሆነውን እንስሳ መልካም ባልሆነው፣ መልካም ያልሆነውንም መልካም በሆነው አይለውጥ ወይም አይተካ፤ አንዱን እንስሳ በሌላው ከተካም ሁለቱ የተቀደሱ ይሆናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መልካሙን በክፉ ወይም ክፉውን በመልካም ቢሆንም እንኳ እርሱን በሌላ አትተካ ወይንም አትለውጥ፤ እንስሳንም በእንስሳ ቢለውጥ እርሱና ልዋጩ ሁለቱም የተቀደሱ ይሆናሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰውየውም ለዚያ እንስሳ ሌላ ምትክ ማቅረብ አይገባውም፤ ምትክ አቅርቦ በተገኘ ጊዜ ግን ሁለቱም እንስሶች ለእግዚአብሔር የተለዩ ይሁኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መልካሙን በክፉ፥ ክፉውንም በመልካም አይለውጥ፤ እንስሳንም በእንስሳ ቢለውጥ እርሱና ልዋጩ የተቀደሱ ይሆናሉ። |
“ለእግዚአብሔርም መሥዋዕት አድርጎ የሚያቀርበው እንስሳ ቢሆን፥ ሰው ከእነዚህ ለእግዚአብሔር የሚሰጠው ሁሉ ቅዱስ ይሆናል።