“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብላችሁ ንገሩአቸው፦ በምድር ካሉት እንስሳት ሁሉ የምትበሉአቸው እንስሳት እነዚህ ናቸው።
ዘሌዋውያን 11:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ከሚበርሩት፥ አራትም እግሮች ካሉአቸው፥ ከእግሮቻቸውም በላይ በምድር ላይ የሚዘልሉባቸው ጭኖች ካሉአቸው ተንቀሳቃሾች እነዚህን ትበላላችሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ክንፍ ኖሯቸው በአራት እግር ከሚንቀሳቀሱ ነፍሳት መካከል ከምድር በሚፈናጠሩበት እግራቸው አንጓ ያለባቸውን መብላት ትችላላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ከእግሮቻቸው በላይ በምድር ላይ የሚዘሉባቸው ጭኖች ካሉአቸው፥ በአራት እግሮች ከሚሄዱ ጥቃቅን በራሪ ነፍሳት እነዚህን ትበላላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ከእነርሱ መካከል ከእግሮቻቸው በላይ በምድር ላይ የሚዘሉባቸው ቅልጥሞች ካሉአቸው ተንቀሳቃሾች እነዚህን ትበላላችሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ከሚበርሩት፥ አራትም እግሮች ካሉአቸው፥ ከእግሮቻቸውም በላይ በምድር ላይ የሚዘልሉባቸው ጭኖች ካሉአቸው ተንቀሳቃሾች እነዚህን ትበላላችሁ። |
“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብላችሁ ንገሩአቸው፦ በምድር ካሉት እንስሳት ሁሉ የምትበሉአቸው እንስሳት እነዚህ ናቸው።
ከእነርሱም እነዚህን አትበሉም፤ ኩብኩባ የሚመስለውም፥ ፌንጣ የሚመስለውም፥ አሸን የሚመስለውም፥ አንበጣ የሚመስለውም።