ሰቈቃወ 3:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሌፍ። በቍጣው በትር ችግር ያየ ሰው እኔ ነኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በቍጣው በትር፣ መከራ ያየ ሰው እኔ ነኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሌፍ። በቁጣው በትር መከራ ያየ ሰው እኔ ነኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአምላክ የቊጣ በትር መከራን ያየሁ እኔ ነኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሌፍ። በቍጣው በትር መከራ ያየ ሰው እኔ ነኝ። |
መልኩም የተናቀ፥ ከሰውም ልጆች ሁሉ የተዋረደ፥ የተገረፈ ሰው፥ መከራንም የተቀበለ ነው፤ ፊቱንም መልሶአልና አቃለሉት፥ አላከበሩትምም።
ኤርምያስንም ወሰዱት፤ በግዞት ቤትም አደባባይ ወደ ነበረው ወደ ንጉሡ ልጅ ወደ መልክያ ጕድጓድ ውስጥ ጣሉት፤ ኤርምያስንም በገመድ አወረዱት። በጕድጓዱም ውስጥ ጭቃ እንጂ ውኃ አልነበረበትም፤ ኤርምያስም ወደ ጭቃው ውስጥ ገባ።
ወንዶችንና ሴቶችን፥ ሕፃናቱንም፥ የንጉሡንም ሴቶች ልጆች፥ የአዛዦችም አለቃ ናቡዛርዳን ከሳፋን ልጅ ከአኪቃም ልጅ ከጎዶልያስ ጋር የተዋቸውን ሰዎች ሁሉ፥ ነቢዩ ኤርምያስንና የኔርዩን ልጅ ባሮክንም ወሰዱ።
በሕዝቤ ሴት ልጅ ስብራት እኔ ወድቄ ተሰብሬአለሁ፤ ጠቍሬማለሁ፤ ራስ ማዞርም ይዞኛል፤ ምጥ እንደያዛትም ሴት በመከራው እጨነቃለሁ።