ዮዲትም አለች፥ “አምላኬን በከበሮ አመስግኑት፤ ለጌታዬም በጸናጽል ዘምሩለት፤ በገና እየደረደራችሁ አመስግኑት፤ በምስጋና ከፍ ከፍ አድርጉት። ስሙንም ጥሩ፤
ጌታ ሰልፍን የሚሰብር አምላክ ነውና፤ የጦር ሰፈሩን በሕዝቡ መካከል አደረገ፤ ከሚያሳድዱኝም ሰዎች እጅ አዳነኝ።