ሁሉም ከእርስዋ ዘንድ ወጡ፤ ታናሽም፥ ታላቅም ቢሆን በእልፍኙ የቀረ አልነበረም። ዮዲትም ተነሥታ በመኝታው አጠገብ ቆመች። በልቧም፥ “የኀይል ሁሉ አምላክ አቤቱ፥ ይህን ነገር እይ፤ ኢየሩሳሌም ከፍ ከፍ ትል ዘንድ በዚች ሰዓት በእኔ እጅ ኀይልህን አድርግ።
ሁሉም ከፊትዋ ወጡ፥ ከትንሽ እስከ ትልቅ ማንም በመኝታ ቤቱ የቀረ አልነበረም። ዮዲት በአልጋው አጠገብ ቆመች፥ በልቧም እንዲህ አለች፦ “የኃይል ሁሉ አምላክ ጌታ ሆይ ስለ ኢየሩሳሌም ክብር በዚች ሰዓት በእጄ የማደርገውን ስራ ተመልከት።