በመሸም ጊዜ አሽከሮቹ ፈጥነው ሰውን አስወጡ፤ ባግዋም ከወደ ውጭ በላያቸው ድንኳኑን ዘጋ፤ በጌታውም ፊት የቆሙ አሽከሮቹን አስወጥቶ ሰደዳቸው፤ ፈጽመው ስለጠጡ ሁሉም ደክመዋልና ወደ ማደሪያቸው ገቡ።
በመሸም ጊዜ ባርያዎቹ ተጣድፈው ወጡ፤ ባጎስም ድንኳኑን ከውጭ ዘጋ፥ በጌታው ፊት ያሉ አሽከሮችንም አስወጣቸው፤ ብዙ ጠጥተው ሁሉም ተዳከመው ነበርና ወደ ማደሪያቸው ገቡ።