La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መሳፍንት 2:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እኔም የነዌ ልጅ ኢያሱ ትቶ​አ​ቸው ከአ​ለፈ አሕ​ዛብ አን​ዱን ሰው እን​ኳን ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ከፊ​ታ​ቸው አላ​ወ​ጣም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ኢያሱ በሞተ ጊዜ ከተዋቸው በምድሪቱ ከነበሩት ሕዝቦች አንዳቸውንም እንኳ በፊታቸው አሳድጄ አላስወጣም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ኢያሱ በሞተ ጊዜ ከተዋቸው በምድሪቱ ከነበሩት ሕዝቦች አንዳቸውንም በፊታቸው አሳድጄ አላስወጣም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህ ኢያሱ በሞተ ጊዜ በምድሪቱ የነበሩትን ሰዎች አንዳቸውንም አላስወጣላቸውም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ይሄዱባት ዘንድ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ወይም አይጠብቁ እንደ ሆነ እስራኤልን እፈትንባቸው ዘንድ፥ ኢያሱ በሞተ ጊዜ ከተዋቸው አሕዛብ አንዱን ሰው እንኳ ከእንግዲህ ወዲህ ከፊታቸው አላወጣም።

Ver Capítulo



መሳፍንት 2:21
8 Referencias Cruzadas  

ፍር​ዴን አላ​ደ​ረ​ጉ​ምና፥ ሥር​ዐ​ቴ​ንም ጥሰ​ዋ​ልና፥ ሰን​በ​ታ​ቴ​ንም አር​ክ​ሰ​ዋ​ልና፥ ዐይ​ኖ​ቻ​ቸ​ውም የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ዐሳብ ተከ​ት​ለ​ዋ​ልና።


አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰ​ጣ​ችሁ ከዚ​ህች ከመ​ል​ካ​ሚቱ ምድር እስ​ክ​ት​ጠፉ ድረስ መው​ደ​ቂ​ያና ወጥ​መድ፥ በእ​ግ​ራ​ች​ሁም ችን​ካር፥ በዐ​ይ​ና​ች​ሁም እሾህ ይሆ​ኑ​ባ​ች​ኋል እንጂ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲያ እነ​ዚ​ህን አሕ​ዛብ ከፊ​ታ​ችሁ እን​ዳ​ያ​ጠ​ፋ​ቸው ራሳ​ችሁ ዕወቁ።


እነሆ እኔ ካጠ​ፋ​ኋ​ቸው አሕ​ዛብ ሁሉ ጋር ከዮ​ር​ዳ​ኖስ ጀምሮ በፀ​ሐይ መግ​ቢያ እስ​ካ​ለው እስከ ታላቁ ባሕር ድረስ ለነ​ገ​ዶ​ቻ​ችሁ ርስት እን​ዲ​ሆኑ የቀ​ሩ​ትን እነ​ዚ​ህን አሕ​ዛብ በዕጣ ከፈ​ል​ሁ​ላ​ችሁ።


አም​ላ​ካ​ች​ሁም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ ከፊ​ታ​ችሁ እስ​ኪ​ደ​መ​ሰሱ ድረስ ያጠ​ፋ​ላ​ች​ኋል፤ ከፊ​ታ​ች​ሁም እነ​ር​ሱ​ንና ንጉ​ሦ​ቻ​ቸ​ውን እስ​ኪ​ያ​ጠ​ፋ​ቸው ድረስ የዱር አራ​ዊ​ትን ይሰ​ድ​ድ​ባ​ቸ​ዋል፤ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገረ ምድ​ራ​ቸ​ውን ትወ​ር​ሳ​ላ​ችሁ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ኢያሱ ከሞተ በኋላ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች፥ “ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንን የሚ​ወ​ጋ​ልን ማን አለቃ ይወ​ጣ​ል​ናል?” ብለው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠየቁ።


ስለ​ዚ​ህም እኔ አሕ​ዛ​ብን ከፊ​ታ​ችሁ አላ​ወ​ጣ​ቸ​ውም፤ ነገር ግን ያስ​ጨ​ን​ቋ​ች​ኋል፤ አማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ወጥ​መድ ይሆ​ኑ​ባ​ች​ኋል” አልሁ።


የከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያ​ን​ንም ጦር​ነት ሁሉ ያላ​ወ​ቁ​ትን እስ​ራ​ኤ​ልን በእ​ነ​ርሱ ይፈ​ት​ና​ቸው ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እነ​ዚ​ህን አሕ​ዛብ ተዋ​ቸው።


እነ​ር​ሱም አም​ስቱ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን መኳ​ን​ንት፥ ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንም ሁሉ ፥ ሲዶ​ና​ው​ያ​ንም፥ ከበ​ዓ​ል​ሄ​ር​ሞን ተራራ ጀምሮ እስከ ኤማት መግ​ቢያ ድረስ በሊ​ባ​ኖስ ተራራ የሚ​ኖ​ሩ​ትም ኤዌ​ዎ​ና​ው​ያን፤