ሁሉም እያንዳንዱ በፊቱ የነበረውን ሰው ገደለ፤ ደጋግመውም ገደሉ። ከዚህም በኋላ ሶርያውያን ሸሹ፤ እስራኤልም አሳደዱአቸው፤ የሶርያ ንጉሥ ወልደ አዴርም በፈጣን ፈረስ አመለጠ።
መሳፍንት 16:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደሊላም የልቡን ሁሉ እንደ ነገራት ባወቀች ጊዜ፥ “የልቡን ሁሉ ነግሮኛልና ይህን ጊዜ ደግሞ ኑ” ብላ ላከችና የፍልስጥኤማውያንን መሳፍንት ጠራች። የፍልስጥኤማውያንም መሳፍንት ብሩን በእጃቸው ይዘው ወደ እርስዋ መጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደሊላ ሁሉንም ነገር እንደ ነገራት በተረዳች ጊዜ፣ ለፍልስጥኤማውያን ገዦች “ሁሉንም ነገር ነግሮኛልና ተመልሳችሁ ኑ” ብላ ላከችባቸው፤ የፍልስጥኤማውያን ገዦችም ብሩን ይዘው ተመልሰው መጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደሊላ ሁሉንም ነገር እንደ ነገራት በተረዳች ጊዜ፥ ለፍልስጥኤማውያን ገዦች “ሁሉንም ነገር ነግሮኛልና ተመልሳችሁ ኑ” ብላ ላከችባቸው፤ የፍልስጥኤማውያን ገዦችም ብሩን ይዘው ተመልሰው መጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደሊላ እውነቱን እንደ ነገራት በተረዳች ጊዜ “እውነቱን ስለ ነገረኝ አንድ ጊዜ ተመልሳችሁ ኑ” ስትል ወደ ፍልስጥኤማውያን ገዢዎች መልእክት ላከች። እነርሱም ብሩን ይዘው መጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደሊላም የልቡን ሁሉ እንደ ገለጠላት ባየች ጊዜ፦ የልቡን ሁሉ ገልጦልኛልና ይህን ጊዜ ደግሞ ኑ ብላ ላከችና የፍልስጥኤማውያንን መኳንንት ጠራች። የፍልስጥኤማውያን መኳንንትም ብሩን በእጃቸው ይዘው ወደ እርስዋ መጡ። |
ሁሉም እያንዳንዱ በፊቱ የነበረውን ሰው ገደለ፤ ደጋግመውም ገደሉ። ከዚህም በኋላ ሶርያውያን ሸሹ፤ እስራኤልም አሳደዱአቸው፤ የሶርያ ንጉሥ ወልደ አዴርም በፈጣን ፈረስ አመለጠ።
የሞዓብ ሽማግሌዎችና የምድያም ሽማግሌዎችም የምዋርቱን ዋጋ በእጃቸው ይዘው ሄዱ፤ ወደ በለዓምም መጡ፤ የባላቅንም ቃል ነገሩት።
ሴሰኛ፥ ወይም ኀጢአተኛ፥ ወይም ቀማኛ፥ ወይም ጣዖትን የሚያመልክ ሁሉ በእግዚአብሔር ልጅ በክርስቶስ መንግሥት ዕድል ፋንታ እንደሌለው ይህን ዕወቁ።
እርሱም፥ “ከእናቴ ማኅፀን ጀምሬ ለእግዚአብሔር ናዝራዊ ነኝና ራሴን ምላጭ አልነካኝም፤ የራሴንም ጠጕር ብላጭ ኀይሌ ከእኔ ይነሣል፤ እደክማለሁም፤ እንደ ሌላም ሰው ሁሉ እሆናለሁ” ብሎ የልቡን ሁሉ ነገራት።
እርስዋም በጕልበቷ ላይ አስተኛችው፤ ጠጕር ቈራጭም ጠራች፤ እርሱም ሰባቱን የራሱን ጕንጕን ላጨው። ይደክምም ጀመረ፤ ኀይሉም ከእርሱ ሄደ።
የፍልስጥኤማውያን መሳፍንትም ወደ እርስዋ ወጥተው፥ “እርሱን አባብለሽ በእርሱ ያለ ታላቅ ኀይል በምን እንደ ሆነ፥ እኛም እርሱን ለማዋረድ እናስረው ዘንድ የምናሸንፈው በምን እንደ ሆነ ዕወቂ፤ እኛም እያንዳንዳችን ሺህ አንድ መቶ ብር እንሰጥሻለን” አሉአት።