መሳፍንት 12:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም፥ “አሁን ሺቦሌት በሉ” አሉአቸው፤ እነርሱም አጥርተው መናገር አልቻሉምና፥ “ሲቦሌት” አሉ፤ ይዘውም በዮርዳኖስ መሸጋገርያ አረዱአቸው፤ በዚያም ጊዜ ከኤፍሬም አርባ ሁለት ሺህ ሰዎች ወደቁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስኪ “ሺቦሌት” በል ይሉታል፤ ቃሉን በትክክል ማለት ሳይችል ቀርቶ “ሲቦሊት” ካለ፣ ይዘው እዚያው እመልካው ላይ ይገድሉታል። በዚያ ጊዜም አርባ ሁለት ሺሕ ኤፍሬማውያን ተገደሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስቲ “ሺቦሌት” በል ይሉታል፤ ታዲያ ቃሉን በትክክል ማለት ሳይችል ቀርቶ “ሲቦሊት” ካለ ይዘው እዚያው መሻገርያው ላይ ይገድሉታል፤ በዚያ ጊዜም አርባ ሁለት ሺህ ኤፍሬማውያን ተገደሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እስቲ ሺቦሌት” በል ይሉታል፤ እርሱ ግን “ሺ” የሚለውን ፊደል አስተካክሎ መናገር ስለማይችል “ሲቦሌት” ይላል፤ ከዚህ በኋላ እርሱን ይዘው የዮርዳኖስ መሸጋገሪያ ከሆኑት ስፍራዎች በአንዱ ይገድሉታል፤ ያንጊዜም በዚሁ ዐይነት አርባ ሁለት ሺህ የኤፍሬም ሰዎች ተገደሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱ፦ አሁን ሺቦሌት በል አሉት፥ እርሱም አጥርቶ መናገር አልቻለምና፦ ሲቦሌት አለ፥ ይዘውም በዮርዳኖስ መሻገርያ አረዱት፥ በዚያም ጊዜ ከኤፍሬም አርባ ሁለት ሺህ ሰዎች ወደቁ። |
በዚያ ቀን እንዲህ ይሆናል፤ እግዚአብሔር ከወንዝ ፈሳሽ ጀምሮ እስከ ግብፅ ወንዝ ድረስ ዐጥር ያጥራል፤ እናንተም የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ አንድ በአንድ ትሰበሰባላችሁ።
ኢየሱስ ግን አሳባቸውን አውቆ እንዲህ አላቸው “እርስ በርስዋ የምትለያይ መንግሥት ሁላ ትጠፋለች፤” እርስ በርሱ የሚለያይ ከተማም ሁሉ ወይም ቤት አይቆምም።
የገለዓድ ሰዎችም ኤፍሬም በሚያልፍበት በዮርዳኖስ ማዶ ደረሱባቸው። ከዚህ በኋላ ከኤፍሬም ያመለጡት እንሻገር ባሉ ጊዜ የገለዓድ ሰዎች፥ “በውኑ እናንተ ከኤፍሬም ወገን ናችሁን?” ቢሉአቸው “አይደለንም” አሉ።