ከንፍታሌምም ነገድ በገሊላ ያለችው ቃዴስና መሰማሪያዋ፥ ሐሞንና መሰማሪያዋ፥ ቄርያታይምና መሰማሪያዋ ተሰጡ።
ኢያሱ 21:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከንፍታሌምም ነገድ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነችውን በገሊላ ውስጥ ቃዴስንና መሰማርያዋን፥ ኤማትንና መሰማርያዋን፥ ቃርቴንንና መሰማሪያዋን፤ ሦስቱን ከተሞች ሰጡአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከንፍታሌም ነገድ፣ በገሊላ ውስጥ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ የሆነችው ከተማ ቃዴስ፣ ሐሞትዶርና ቀርታን እነዚህ ሦስት ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከንፍታሌምም ነገድ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነችውን በገሊላ ውስጥ ቃዴስንና መሰማሪያዋን፥ ሐሞት-ዶንና መሰማሪያዋን፥ ቀርታንንና መሰማሪያዋን፤ ሦስቱን ከተሞች ሰጡአቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከንፍታሌም ግዛት ተከፍለው ከግጦሽ ምድራቸው ጋር የተሰጡአቸው ሦስት ከተሞች በገሊላ ከመማጸኛ ከተሞች አንድዋ የሆነችው ቄዴሽ፥ ሐሞት፥ ዶርና ቃርታን ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከንፍታሌምም ነገድ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነቸውን በገሊላ ውስጥ ቃዴስንና መሰምርያዋን፥ ሐሞትዶንና መሰምርያዋን፥ ቀርታንንና መሰምርያዋን፥ ሦስቱን ከተሞች ሰጡአቸው። |
ከንፍታሌምም ነገድ በገሊላ ያለችው ቃዴስና መሰማሪያዋ፥ ሐሞንና መሰማሪያዋ፥ ቄርያታይምና መሰማሪያዋ ተሰጡ።
በንፍታሌም ባለው በተራራማው ሀገር በገሊላ ቃዴስን፥ በኤፍሬምም ባለው በተራራማው ሀገር ሴኬምን፥ በይሁዳም ባለው በተራራማው ሀገር ኬብሮን የምትባለውን የአርቦቅን ከተማ ለዩ።
ዲቦራም ልካ ከቃዴስ ንፍታሌም የአቢኒሔምን ልጅ ባርቅን ጠርታ እንዲህ አለችው፥ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ያዘዘህ አይደለምን? ሄደህ ወደ ታቦር ተራራ ውጣ፤ ከአንተም ጋር ከንፍታሌምና ከዛብሎን ልጆች ዐሥር ሺህ ሰዎች ውሰድ፤