አሜስያስ ግን አልሰማም፤ የእስራኤልም ንጉሥ ዮአስ ዘመተ፤ እርሱና የይሁዳ ንጉሥ አሜስያስም በይሁዳ ባለች በቤትሳሚስ ፊት ለፊት ተያዩ።
ኢያሱ 19:38 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቄሮህ፥ ሚጋላህሪም፥ ቤታሚና፥ ቴስሚስ፤ ዐሥራ ዘጠኝ መንደሮችና ከተሞቻቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይርኦን፣ ሚግዳልኤል፣ ሖሬም፣ ቤትዓናትና ቤትሳሚስ። እነዚህ ከነመንደሮቻቸው ዐሥራ ዘጠኝ ከተሞች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይርኦን፥ ሚግዳል-ኤል፥ ሖሬም፥ ቤት-ዓናት፥ ቤት-ሳሚስ፤ ዐሥራ ዘጠኝ ከተሞችና መንደሮቻቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይርኦን፥ ሚግዳልኤል፥ ሖሬም፥ ቤትዐናትና ቤትሼሜሽ ተብለው የሚጠሩ ዐሥራ ዘጠኝ ከተሞች በዙሪያቸው ታናናሽ ከተሞች ጋር በዚህ ክልል ውስጥ ይገኛሉ፤ |
አሜስያስ ግን አልሰማም፤ የእስራኤልም ንጉሥ ዮአስ ዘመተ፤ እርሱና የይሁዳ ንጉሥ አሜስያስም በይሁዳ ባለች በቤትሳሚስ ፊት ለፊት ተያዩ።
ድንበሩም ከበኣላ በባሕር በኩል ያልፋል፤ ከዚያም በኢያሪም ከተማ ደቡብ በኩልና በኪስሎን ሰሜን በኩል ወደ አሥራቱስ ድንበር ያልፋል፤ በፀሐይ ከተማም ላይ ይወርዳል፤ በሊባም በኩል ያልፋል።
ድንበራቸውም ወደ ታቦርና ወደ ሰሌም፥ በምዕራብ በኩል ወደ ቤተሳሚስ ይደርሳል፤ የድንበራቸው መውጫም ዮርዳኖስ ነበረ፤ ዐሥራ ስድስት ከተሞችና መንደሮቻቸውም።
ንፍታሌምም የቤትሳሚስንና የቤቴኔስን ሰዎች አላጠፋቸውም፤ በምድሩም በተቀመጡት በከነዓናውያን መካከል ተቀመጡ፤ ነገር ግን በቤትሳሚስና በቤቴኔስ የሚኖሩ ሰዎች ገባሮች ሁኑላቸው።