La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 10:37 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እር​ስ​ዋ​ንም፥ ንጉ​ሥ​ዋ​ንም፥ ከተ​ሞ​ች​ዋ​ንም ሁሉ፥ በእ​ር​ስ​ዋም ያሉ​ትን ነፍ​ሳት ሁሉ በሰ​ይፍ ስለት መቱ፤ በአ​ዶ​ላም እን​ዳ​ደ​ረ​ገው ሁሉ ማን​ንም አላ​ስ​ቀ​ረም ፤ እር​ስ​ዋ​ንም፥ በእ​ር​ስ​ዋም ያሉ​ትን ነፍ​ሳት ሁሉ ፈጽሞ አጠፋ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከተማዪቱንም ከንጉሧ፣ ከመንደሮቿና በውስጧ ካሉት ጋራ ሁሉ አንድም ሰው ሳያስቀሩ በሰይፍ ስለት ፈጇቸው፤ በዔግሎን እንዳደረጉት ሁሉ እዚህም ከተማዪቱንና በውስጧ ያለውን ሁሉ ፈጽመው ደመሰሱ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ያዙአትም፤ እርሷንም ንጉሥዋንም ከተሞችዋንም ሁሉ በእርሷም ያሉትን ሰዎች ሁሉ በሰይፍ ስለት መቱ፤ በዔግሎም እንዳደረገው ሁሉ ማንንም አላስቀረም፤ እርሷንም በእርሷም ያሉትን ሰዎች ሁሉ ፈጽሞ አጠፋ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እርስዋንም ይዘው ንጉሡን፥ በከተማይቱና በአካባቢዋም የገጠር ከተሞች ያገኙትን ሁሉ ገደሉ፤ ኢያሱም ልክ በዔግሎን ባደረገው ዐይነት ከተማይቱ እንድትደመሰስ ፈረደባት፤ በእርስዋም ውስጥ በሕይወት የተረፈ አንድም አልነበረም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እርስዋንም ንጉሥዋንም ከተሞችዋንም ሁሉ በእርስዋም ያሉትን ነፍሳት ሁሉ በሰይፍ ስለት መቱ፥ በኦዶላም እንዳደረገው ሁሉ ማንንም አላስቀረም፥ እርስዋንም በእርስዋም ያሉትን ነፍሳት ሁሉ ፈጽሞ አጠፋ።

Ver Capítulo



ኢያሱ 10:37
8 Referencias Cruzadas  

ኢያ​ሱም ዐማ​ሌ​ቅ​ንና ሕዝ​ቡን በሰ​ይፍ ስለት አሸ​ነፈ።


በዚ​ያም ቀን መቄ​ዳን ያዟት፤ እር​ስ​ዋ​ንና ንጉ​ሥ​ዋ​ንም በሰ​ይፍ ስለት ገደሉ፤ በእ​ር​ስ​ዋም ያሉ​ትን ነፍ​ሳት ሁሉ ፈጽ​መው አጠ​ፉ​አ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም አን​ዱን ስንኳ አላ​ስ​ቀ​ሩም፤ የዳ​ነም፥ ያመ​ለ​ጠም የለም፤ በኢ​ያ​ሪ​ኮም ንጉሥ እን​ዳ​ደ​ረጉ በመ​ቄዳ ንጉሥ አደ​ረጉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ር​ኤል እጅ አሳ​ልፎ ሰጣት፤ በዚ​ያም ቀን ያዙ​አት፤ በሰ​ይ​ፍም ስለት መቱ​አት፤ በላ​ኪ​ስም እን​ዳ​ደ​ረ​ገው ሁሉ፥ በእ​ር​ስዋ ያሉ​ትን ነፍ​ሳት ሁሉ ፈጽሞ አጠፋ።


ኢያ​ሱም ከእ​ር​ሱም ጋር እስ​ራ​ኤል ሁሉ ከአ​ዶ​ላም ወደ ኬብ​ሮን ወጡ፤ ወጉ​አ​ትም፤ ያዙ​አ​ትም፤


ኢያ​ሱም፥ ከእ​ር​ሱም ጋር እስ​ራ​ኤል ሁሉ ወደ ዳቤር ተመ​ለሱ፤ ወጉ​አ​ትም፤


እር​ስ​ዋ​ንም፥ ንጉ​ሥ​ዋ​ንም፥ ከተ​ሞ​ች​ዋ​ንም ያዙ፤ በሰ​ይ​ፍም ስለት መቱ​አ​ቸው፤ በእ​ነ​ር​ሱም ውስጥ ያሉ​ትን ነፍ​ሳት ሁሉ ፈጽ​መው አጠፉ፤ ማን​ንም አላ​ስ​ቀ​ረም፤ በኬ​ብ​ሮ​ንና በን​ጉ​ሥ​ዋም እን​ዳ​ደ​ረ​ገው እን​ዲሁ በዳ​ቤ​ርና በን​ጉ​ሥዋ አደ​ረገ።


እን​ዲ​ሁም ኢያሱ ምድ​ሪ​ቱን ሁሉ፥ ተራ​ራ​ማ​ውን ሀገር፥ ደቡ​ቡ​ንም፥ ቆላ​ው​ንም፥ ቍል​ቍ​ለ​ቱ​ንም፥ ንጉ​ሦ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሁሉ መታ፤ ማን​ንም አላ​ስ​ቀ​ረም፤ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘ​ውም ነፍስ ያለ​በ​ትን ሁሉ ፈጽሞ አጠፋ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አገ​ል​ጋይ ሙሴ እን​ዳ​ዘ​ዘው፥ ኢያሱ የእ​ነ​ዚ​ህን መን​ግ​ሥ​ታት ከተ​ሞች ሁሉ፥ ንጉ​ሦ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሁሉ ያዘ፤ በሰ​ይ​ፍም መታ​ቸው፤ ፈጽ​ሞም አጠ​ፋ​ቸው።