La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዮሐንስ 7:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ጊዜዬ ገና አል​ደ​ረ​ሰም፤ የእ​ና​ንተ ጊዜ ግን ዘወ​ትር የተ​ዘ​ጋጀ ነው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “ለእኔ ትክክለኛው ጊዜ ገና አልደረሰም፤ ለእናንተ ግን ማንኛውም ጊዜ ምቹ ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ኢየሱስም እንዲህ አላቸው “ጊዜዬ ገና አልደረሰም፤ ጊዜያችሁ ግን ዘወትር የተመቸ ነው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “የእኔ ጊዜ ገና አልደረሰም፤ የእናንተ ጊዜ ግን ዘወትር የተመቸ ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “ጊዜዬ ገና አልደረሰም፥ ጊዜያችሁ ግን ዘወትር የተመቸ ነው።

Ver Capítulo



ዮሐንስ 7:6
10 Referencias Cruzadas  

አባት ለል​ጆቹ እን​ደ​ሚ​ራራ፥ እን​ዲሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሚ​ፈ​ሩት ይራ​ራ​ላ​ቸ​ዋል፤


እርሱም “ወደ ከተማ ከእገሌ ዘንድ ሄዳችሁ ‘መምህር ጊዜዬ ቀርቦአል፤ ከደቀ መዛሙርቴ ጋር ከአንተ ዘንድ ፋሲካን አደርጋለሁ ይላል’ በሉት፤” አለ።


ከፋ​ሲካ በዓል አስ​ቀ​ድሞ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከዚህ ዓለም ወደ ላከው ወደ አብ ይሄድ ዘንድ ጊዜው እንደ ደረሰ ባወቀ ጊዜ በዓ​ለም ያሉ​ትን የወ​ደ​ዳ​ቸ​ውን ወገ​ኖ​ቹን ፈጽሞ ወደ​ዳ​ቸው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ይህን ነገር ተና​ግሮ ዐይ​ኖ​ቹን ወደ ሰማይ አነ​ሣና እን​ዲህ አለ፥ “አባት ሆይ፥ ሰዓቱ ደር​ሶ​አ​ልና ልጅህ ያከ​ብ​ርህ ዘንድ ልጅ​ህን አክ​ብ​ረው፤


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “አንቺ ሆይ ካንቺ ጋር ምን አለኝ? ጊዜዬ ገና አል​ደ​ረ​ሰም” አላት።


ስለ​ዚ​ህም ሊይ​ዙት ወደው ነበር፤ ነገር ግን እጁን በእ​ርሱ ላይ ያነሣ የለም፤ ጊዜዉ ገና አል​ደ​ረ​ሰም ነበ​ርና።


እና​ን​ተም ወደ​ዚህ በዓል ውጡ፤ እኔ አሁን ወደ​ዚህ በዓል አል​ወ​ጣም፤ ጊዜዬ ገና አል​ደ​ረ​ሰ​ምና።”


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በቤተ መቅ​ደስ ሲያ​ስ​ተ​ም​ራ​ቸው በሙ​ዳየ ምጽ​ዋት አጠ​ገብ ይህን ተና​ገ​ራ​ቸው፤ ነገር ግን አል​ያ​ዙ​ትም፤ ጊዜው ገና አል​ደ​ረ​ሰም ነበ​ርና።


እር​ሱም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “አብ በገዛ ሥል​ጣኑ የወ​ሰ​ነ​ውን ቀኑ​ንና ዘመ​ኑን ልታ​ውቁ አል​ተ​ፈ​ቀ​ደ​ላ​ች​ሁም።