ዮሐንስ 21:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ምድርም በወረዱ ጊዜ ፍሙ መርቶ፥ ዓሣም በላዩ ሆኖ፥ እንጀራም ተሠርቶ አገኙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ምድርም በደረሱ ጊዜ፣ ዓሣ በላዩ የነበረበት የከሰል ፍምና እንጀራ አዩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ የብስ በወጡ ጊዜ ዓሣ በላዩ የተቀመጠበት ፍምና እንጀራ አዩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከጀልባው በወረዱ ጊዜ ዓሣ በላዩ የነበረበት የከሰል ፍምና እንጀራ አዩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ምድርም በወጡ ጊዜ ፍምና ዓሣ በላዩ ተቀምጦ እንጀራም አዩ። |
አገልጋዮችና ሎሌዎችም በዚያ ቆመው እሳት አንድደው ይሞቁ ነበር፤ የዚያች ሌሊት ብርድ ጽኑ ነበርና፤ ጴጥሮስም ከእነርሱ ጋር ቆሞ ይሞቅ ነበረ።
ሌሎች ደቀ መዛሙርት ግን በታንኳ መጡ፤ ከሁለት መቶ ክንድ ያህል በቀር ከምድር አልራቁም ነበርና፤ ዓሣ የመላባቸውን መረቦቻቸውንም እየሳቡ ሄዱ።
ጌታችን ኢየሱስም ያን እንጀራ ይዞ አመሰገነ፤ ቈርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው፤ ደቀ መዛሙርቱም ለተቀመጡት ሰዎች ሰጡአቸው፤ ከዓሣውም እንዲሁ የፈለጉትን ያህል ሰጡአቸው።