ዮሐንስ 18:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስምዖን ጴጥሮስም ሾተል ነበረው፤ ሾተሉንም መዝዞ የሊቀ ካህናቱን አገልጋይ መትቶ ቀኝ ጆሮውን ቈረጠው፤ የዚህም አገልጋይ ስም ማልኮስ ይባል ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰይፍ ይዞ የነበረው ስምዖን ጴጥሮስም፣ ሰይፉን መዝዞ የሊቀ ካህናቱን ባሪያ ቀኝ ጆሮ ቈረጠ፤ የባሪያውም ስም ማልኮስ ይባል ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስምዖን ጴጥሮስም ሰይፍ ይዞ ስለ ነበር መዘዘውና የሊቀ ካህናቱን አገልጋይ መትቶ ቀኝ ጆሮውን ቈረጠ፤ የአገልጋዩም ስም ማልኮስ ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስምዖን ጴጥሮስ ሰይፍ ይዞ ስለ ነበረ መዘዘና የካህናት አለቃውን አገልጋይ መትቶ ቀኝ ጆሮውን ቈረጠ፤ የአገልጋዩም ስም “ማልኮስ” ይባል ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስምዖን ጴጥሮስም ሰይፍ ስለ ነበረው መዘዘው፥ የሊቀ ካህናቱንም ባርያ መትቶ ቀኝ ጆሮውን ቈረጠ፤ የባርያውም ስም ማልኮስ ነበረ። |
ጴጥሮስ ጆሮውን ከቈረጠው ሰው ዘመዶች ወገን የሆነ ከሊቀ ካህናቱ አገልጋዮችም አንድ ሰው፥ “እኔ በአትክልት ቦታ ውስጥ ከእርሱ ጋር አይችህ አልነበረምን?” አለው።