ዮሐንስ 13:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህንም ዐውቃችሁ ብትሠሩ ብፁዓን ናችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ እነዚህን ነገሮች ዐውቃችሁ ብትፈጽሙ ትባረካላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህንን ስታውቁና ስታደርጉ ብፁዓን ናችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን ነገር ብታውቁና በሥራ ላይ ብታውሉት የተባረካችሁ ናችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህን ብታውቁ፥ ብታደርጉትም ብፁዓን ናችሁ። |
እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፥ “ይህችን ቃል ሁሉ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም አደባባይ ተናገር፤ እንዲህም በል፦ የዚህን ቃል ኪዳን ቃል ስሙ፤ አድርጉትም።
መንፈሴንም በውስጣችሁ አኖራለሁ፤ በትእዛዜም እንድትሄዱ አደርጋችኋለሁ፤ ፍርዴንም ትጠብቃላችሁ ታደርጉትማላችሁ።
በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ በፍቅር የምትሠራ እምነት እንጂ መገዘር አይጠቅምምና፤ አለመገዘርም ግዳጅ አይፈጽምምና።