ኢዮብ 41:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መኝታው እንደ ስለታም ድንጋይ ነው፤ የባሕር ወርቅ ሁሉ በእርሱ ዘንድ እንደማይቈጠር ጭቃ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስትንፋሱ ከሰል ያቀጣጥላል፤ የእሳትም ነበልባል ከአፉ ይወጣል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዱላን እንደ ገለባ ይቈጥረዋል፥ ሰይፎች ሲንቀጠቀጡ ይስቃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የትንፋሹ ግለት ከሰል ያቀጣጥላል፤ የእሳት ነበልባልም ከአፉ ይወጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሎታውን እንደ ገለባ ይቈጥረዋል፥ ሰላጢኑም ሲሰበቅ ይስቃል። |
የእግዚአብሔር ሥርዐት ቅን ነው፥ ልብንም ደስ ያሰኛል፤ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው፥ ዐይኖችንም ያበራል።
ከቀድሞም ጀምሮ የማቃጠያ ስፍራ ተዘጋጅታለች፤ ለንጉሥም ተበጅታለች፤ ጥልቅና ሰፊም አድርጎአታል፤ እሳትና ብዙ ማገዶ ተከምሮአል፤ የእግዚአብሔርም ቍጣ እንደ ዲን ፈሳሽ ያቃጥለዋል።